UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

ተጎድቷል፣ ሰዎች ህክምና ቦታ ተሸክመው እየወሰዱት ነው። ፍልስጤማዊ ታዳጊ ግን አንድ ቃል ደጋግሞ ይናገራል፦

\"በህይወት አለሁ (አልሞትኩት) የመግሪብ ሶላት እንዳያልፈኝ\" የሚለውን ቃል ይደጋግማል። የተሸከሙት ሰዎች ህክምና እንዲያገኝ በማሰብ አካሉን ተሸክመው በመያዛቸው ሶላት ሊያልፍበት እንደሆነ ገምቶ ፍጹም ደስተኛ አይደለም።

አንገቱ አካባቢ የደረሰበትን ጉዳት ለማከም ሲሞክሩም \"ይሄ (ቁስል) አይገድለኝም፣ መግሪብ እንዳያልፈኝ\" ሲል ደጋግሞ ይናገራል።

ድንገት በሞትና በህይወት መካከል ውስጥ ተገኝተው እንኳን ጭንቀታቸው በቶሎ ስለመዳን አይደለም፣ በጨመረው የጥቂት ቀን እድሜያቸውም ቢሆን የሚያሳስባቸው ከአላህ ጋር ያላቸው ንግግር ነው። ሶላትን በዚያ የመከራ ጊዜያቸው ውስጥ እንኳን የልባቸው መርጊያ አድርገው ይዘውታል።

በተመቻቸ ሁኔታ ውስጥ ሶላት መስገድ ያልገራልህ ሙስሊም ወንድሜ ኡዝርህ ምን ይሆን? ከጌታህ ጋር የሚኖርህን ስንቱን መመሳጠርስ በከንቱ መባከኑን ተረዳህ?እስከመቸ ከዚህ ደስታ በፍቃድህ ትሸሻለህ?

Yahya Ibnu Nuhe

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Zinet Ahmed Changed her profile picture
2 months
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አላህ ሆይ የኢማን ጣዕም በኢባዳችን ውስጥ አቅምሰን ያረብ ።

  ህይወት ያለው ሰኪና ያለው  አላህ ጋር ባለን ያማረ

ግንኙነት ነው

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

እንባቸውን እናብስ

7 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Zinet Ahmed shared a
Translation is not possible.

ሐማስ አቅሙን ሳያውቅ ለምን ወደ ጦርነት ገባ⁉️

================================

✍ ዛሬ ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ በኢማሙ አሕመድ መስጅድ በነበረው የፈታዋ ፕሮግራም ላይ «ያለ አቅም ጦርነት መጀመር እንደት ይታያል? ጥቅምና ጉዳትን ማመዛን አይገባም ወይ?» የሚል ይዘት ያለው ጥያቄ ተጠይቆ ነበር። ያው የጥያቄው ዐውድ ወቅታዊውን የሐማስና የእስራኤል ጉዳይ እንደሚያሳይ ግልፅ ይመስለኛል።

ሸይኹም ጠያቂው ከዚህ ተጨባጭ ጋር ማያያዝ እንደፈለገ ስለተረዳ በዚያው አውድ ነው ምላሹን የሰጠው። ይህ ጥያቄ ብዙዎቻችሁ ጋር እንደሚፈጠር ስለገመትኩና እዚሁ ማኅበራዊ ሚዲያም ላይ አልፎ አልፎ ስላጋጠመኝ፤ ቃል በቃል ባይሆንም በይዘት ደረጃ መልሱን ላካፍላችሁ።

√ በመጀመሪያ ደረጃ አንድ ሰው አቅሙ የማይችለውን ነገር ነፍስያውን ማሸከም እንደሌለበት ሓዲሥ አጣቅሶ ካስረዳ በኋላ ጥቅምና ጉዳትን አመዛዝኖ መወሰንም ተገቢ ሸሪዓዊ መርህ መሆኑን ተናግሯል። ይህ የወል እውነታ እንዳለ ሆኖ፤ ነገር ግን ዝርዝር መረጃ በሌለን ጉዳይ ላይ ይህን መርህ እንደወረደ ተግባራዊ አድርጎ ብይን መስጠት ተገቢ አይደለም።

ማለትም በሩቅ ሆነን በሚዲያ በሰማነው ብቻ ተመርኩዘን ሐማስ ጥፋተኛ ነው አንልም። ምናልባትም ሌሎች ሃገሮች እናግዝሃለን ብለው ቃል ገብተውለት በኋላ ከድተውት ሊሆን ይችላል፣ (ወይም ወራ'ሪዋ የተለመደውን ጥቃቱን ልትፈጽምበት መዘጋጀቷን አውቆ ቀድሞ ራሱን ለመከላከል ይሆናል… ብቻ አላሁ አዕለም)።

እንደ ጥቅል ደግሞ መታወቅ ያለበት ነገር ሐማስ ያኔ ኦክቶበር 7 ጥቃት ባይፈጽምም ወራ'ሪዋ ፈለስጢናዊያንን ከማጥቃት አልተወገደችም። ጋዛንም ላለፉት 16 አመታት ገደማ በሽቦ አጥርና በኮንክሪት ዙሪያዋን አጥራ ያለርሷ ፈቃድ ጋዛዊያን መውጣትም ሆነ መግባት አይችሉም። ይህም ጋዛ ጣራ የሌለው የዓለማችን ክፍት እስር ቤት ነው፤ ምዕራባዊያን ራሳቸው ይሄን ያምናሉ።

የወራ'ሪዋ ጋዛዊያንንም ሆነ መላው ፈለስጢናዊያንን የማጥ'ፋትና ከምድራቸው የማስወገድ እቅድ ባለፈ የተጀመረ ሳይሆን ገና ከ1948 በፊት የነበረና ተጠናቅሮ የቀጠለ ፖሊሲ ነው። ስለዚህ ሐማስ ጥቃቱን ጀመረም አልጀመረም ጭካኔዋ የነበረና ያለ ነው።

በቅርበትና በተጨባጩ መረጃ ሳይኖረን ብይን መስጠት የማይገባን መሆኑ እንዳለ ሆኖ ጥፋተኛ ነው ብንል እንኳ ይሄን የቁርኣን አንቀፅ እናስታውስ።

(يَسْأَلُونَكَ عَنِ الشَّهْرِ الْحَرَامِ قِتَالٍ فِيهِ ۖ قُلْ قِتَالٌ فِيهِ كَبِيرٌ ۖ وَصَدٌّ عَن سَبِيلِ اللَّهِ وَكُفْرٌ بِهِ وَالْمَسْجِدِ الْحَرَامِ وَإِخْرَاجُ أَهْلِهِ مِنْهُ أَكْبَرُ عِندَ اللَّهِ ۚ وَالْفِتْنَةُ أَكْبَرُ مِنَ الْقَتْلِ ۗ وَلَا يَزَالُونَ يُقَاتِلُونَكُمْ حَتَّىٰ يَرُدُّوكُمْ عَن دِينِكُمْ إِنِ اسْتَطَاعُوا ۚ …)

"ከተከበረው ወር (ከረጀብ) በርሱ ውስጥ ከመጋደል ይጠይቁሃል፡፡ በላቸው «በርሱ ውስጥ መጋደል ታላቅ (ኀጢአት) ነው፡፡ ግን ከአላህ መንገድ (ሰዎችን) መከላከል፣ በርሱም መካድ፣ ከተከበረውም መስጊድ (ማገድ) ባለቤቶቹንም ከርሱ ማውጣት አላህ ዘንድ ይበልጥ ታላቅ (ወንጀል) ነው፡፡ ፈተናም (ማጋራት) ከመግደል ይበልጥ ከባድ ነው፡፡ (ከሐዲዎች) ቢችሉ ከሃይማኖታችሁ እስከሚመልሳችሁ ድረስ የሚዋጉዋችሁ ከመሆን አይቦዝኑም፡፡…»"

[አል-በቀረህ: 217]

*

√ ጁንዱብ ኢብኑ ዐብደልሏህ ባስተላለፈው ሓዲሥ ላይ፣ ከኢብኑ ዐባስ፣ ከኢብኑ መስዑድና ከዑርዋህ ቢን ዙበይር እንደተዘገበው፤ የዚህ የቁርኣን አንቀፅ የወረደበት ሰበብ፤ ዐብደልሏህ ኢብኑ ጀሕሽ የተባለ ሶሐባ ከሌሎች ባልደረቦቹ ጋር ሆኖ በጧኢፍና በመካህ መካከል ወደምትገኘው ነኽላህ ቁረይሾችን ለመሰለል በውዱ ነቢይ በተላከ ጊዜ መንገዳቸው ላይ ጥፋተኞቹን የቁረይሽ ቅፍለቶች ሲያገኙ ጦር ወረወሩባቸውና ዐምር አል-ሐዽረሚይን ገድ'ለው፤ ኡስርዋ ዑሥማንንና ሐከም ከይሳንን ማረኳቸው።

ታዲያ የዚህን ጊዜ ወሩ የወርሃ ረጀብ የመጀመሪያ ቀን ነበር። ከጁማዱል ኣኺር የመጨረሻ ቀን መስሏቸው ነበርም ተብሏል። ብቻ ወደ ውዱ ነቢይ ተመለሱና ስለሆነው ነገር ሲነግሯቸው፤ ውዱ ነቢይ ጭራሽ በረጀብ ወር እኔ ሰልላችሁ ኑ አልኩ እንጂ ግደ'ሉ ብያለሁ እንደ ብለው ገሰጿቸው።

የቁረይሽ ሙሽሪኮችም «ሙስሊሞች በተከበሩት ወራት (ረጀብ ከተከበሩት ወራት መካከል ስለሆነ) አንጋደልም ይላሉ እንጂ ይሄ ገደሉ አይደል እንደ?» እያሉ ማስወራት ጀመሩ። በነርሱ ቤት ማነወራቸው ነው።

አላህም ይህን ምላሽ ሰጣቸው።

ምንም እንኳ በተከበሩት ወራት መጋ'ደል እርም ቢሆንም፤ ግን ከአላህ መንገድ (ሰዎችን) ከመከላከል፣ በርሱም ከመካድ፣ ከተከበረውም መስጊድ (ከማገድ)፣ ባለቤቶቹንም ከርሱ ከማውጣት አይበልጥም አላቸው። አላህ ዘንድ ይበልጥ ታላቅ (ወንጀል) የናንተ ይህ ሥራችሁ ነው አላቸው፡፡ እናንተ ያላችሁበት ፈተና (በአላህ ላይ ማጋራት) ከመግ'ደል ይበልጥ ከባድ ነው ብሎ መለሰላቸው፡፡

ወደ እኛ ጉዳይ ስናመጣው፤ እንደው ሐማስ አቅምን ካለማወቅና ጥቅምን ከጉዳት ካለማመዛዘን አንፃር ጥፋተኛ ነው ብንል እንኳ (ማለት የለብንም)፤ አይሁዳዊያን እየሠሩት ካለው ግፍ፣ ወረራ፣ ፈሳድ… አንፃር የነርሱ ጥፋት ይበልጥ የከበደ ወንጀል ነው።

በዚህ መስክ እየተገ'ደሉ ያሉ የፈለስጢን ወንድሞቻችን በነፍስ ወከፍ ደረጃ ይሄ ነው ይሄ ነው ባንልም በደፈናው ግን አላህ ከሸሂዶች ጎራ እንደሚመድባቸው ተስፋ እናደርጋለን ብሏል። አላህ ይቀበላቸው፤ ድልንም ያቀዳጃቸው።

እኛም እየሆነ ባለው ነገር ከማዘን የተነሳ ተስፋ መቁረጥ ሳይገባን መጨረሻ ላይ ዲሉ የእኛ መሆኑ በቁርኣንና በሓዲሥ ስለተነገረ በዱዓእ እየበረታን ተስፋችንን ልናለመልም ይገባል፤ ምናልባትም አላህ አይሁዶችን በአሁኑ ወቅት አንድ ቦታ ላይ እንዲሰበሰቡ ያደረጋቸው በቁርኣን ላይ ለተነገረው ቃሉ ሊጠፉ ተቃርበውም ይሆናል የሚል ይዘት ያለው መልዕክት ሲናገር ሰምቻለሁ።

አላሁ አዕለም!

(የቁርኣን አንቀፁን ሰበበ ኑዙል ማንበብ ለምትፈልጉ፦

«جامع البيان» (3/ 650- 660)، و«تفسير ابن أبي حاتم» (2/ 384- 386)، و«أسباب النزول» للواحدي، (ص41)، و«السيرة النبوية» لابن هشام (1/ 601- 605)، و«دلائل النبوة» للبيهقي (3/ 18، 19)، و«تفسير ابن كثير» (1/ 368- 372).)

||

t.me/MuradTadesse

Send as a message
Share on my page
Share in the group