umma1698208858 Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
0
No followings
Translation is not possible.

አንድ ሰው ከአንድ ቤተሰብ የሆነችን ሴት አገባ፤ አንዳንድ የቤተሰቡ አባላት በዘር የሚተላለፍ በሽታ ነበራቸው፤ ይህ ደግሞ በዕድሜ መግፋት የመስማት ችሎታ እያሽቆለቆለ መሄድ ነው!

ባልየው የሚስቱ የመስማት ችሎታ እየደከመ እና እየቀነሰ መምጣቱን ጠረጠረ!!

ይህን የነገረውን የቤተሰብ ሀኪም አማከረ፡- የሚስትህን የመስማት ችሎታ ለማረጋገጥ ቀላል መንገድ አለ እሱም መካከለኛ በሆነ ድምፅ 50 ጫማ ያህል ራቅ ብለክ ትናገራለክ ከዚያም ወደ 40 ጫማ ቀርበህ ትናገራለክ ካልመለሰችልክ ወደ 20 ጫማ ከዚያም ወደ 10 ጫማ ትመጣለህ ካልመለሰች በቃ አጠገቧ ቆመክ ትነግራታለክ በዚህ መልኩ የባለቤትክን የመስማት ችሎታ ጥንካሬ ታረጋግጣለክ።

በእርግጥም ባልየው ወደ ቤት ተመለሰ እናም ሚስቱ ኩሽና ውስጥ ምሳ እያዘጋጀች ነበረ እሱም ከ50 ጫማዋ ርቆ ሄዶ፡- ውዴ ለምሳ ምን እየሰራሽ ነው? አልመለሰችለትም ወደ 40 ጫማ ጠጋ አለና ውዴ ፣ ለምሳ ምን እየሰራሽ ነው?” አልመለሰችለትም ወደ 20 ጫማ ጠጋ ብሎ ጥያቄውን ደገመው እሷ አሁንም አልመለሰችም! ከዚያም ወደ 10 ጫማ ጠጋ ብሎ ጥያቄውን ደገመው አሁንም አልመለሰችለትም!

በመጨረሻም ከኋላዋ ቆሞ፣ ለምሳ ምን እየሰራሽ ነው?” አላት።

ወደ እሱ ዘወር አለችና፡- “ የዶሮ አሩስቶ ” ይህን ስነግርህ ለአምስተኛ ጊዜ ነው!!! አለችው።

ሁልጊዜ አንተ ብቻ ትክክል እንደሆንክ አድርገህ አታስብ ነገሩን በፍትሃዊነት ከተመለከትክ ችግሩ ያንተ እና የአንተ ሊሆን ይችላል❗️❗️❗️

https://t.me/AbuEkrima

https://t.me/AbuEkrima

Send as a message
Share on my page
Share in the group