UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
0
No followings
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ክፍል አንድ

አንደኛ ምክር

ባልሽን ለማስደሰት ብለሽ አላህን አታስቆጪ

በአንቺ እና በአላህ መካከል ያለውን ጉዳይ አስተካክይ ፤በአንቺ ና በሰዎች መካከል ያለውን ጉዳይ አላህ ያስተካክልልሻል::ይህ ህግ አምላካዊ መርህ ነው፡፡ በትዳር ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ሁኔታ ውስጥ የሚተገበር የአላህ ህግ ነው ፡፡ በምንም ጉዳይ ከአላህ እገዛ እና እርዳታ የምትፈልጊ ከሆነ ምንጩን አላህ እንዲህ ሲል ጠቅሶታል፡፡

{يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنْ تَنْصُرُوا اللَّهَ يَنْصُرْكُمْ}[محمد :٧]

{እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ :- አላህን(ሀይማኖቱን) ብትረዱ፤ይረዳችኋል}[ሙሀመድ :7]

﴿ إِنَّ اللَّهَ مَعَ الَّذِينَ اتَّقَوا وَّالَّذِينَ هُم مُّحْسِنُونَ﴾

[ سورة النحل: 128]

{አላህ እሱን ከሚፈሩትና መልካምን ከሚሰሩት ጋር ነው }[ነህል:128]

የሙእሚኖችን ውዴታ ና ፍቅር ከፈለግሽ (በተቃራኒ ፆታ መካከል ያለውን ውዴታ ሳይሆን እንደ እህታቸው እንዲወዱሽና እንዲያከብሩሽ ከፈለግሽ ለማለት ነው ) አላህ እንዲህ ብሎ በቁርአኑ ነግሮሻል፦

﴿ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ سَيَجْعَلُ لَهُمُ الرَّحْمَٰنُ وُدًّا﴾

[ مريم: 96]

{እነዚያ ያመኑ ና አላህ የሚወደውን መልካም ስራ የሰሩ አረህማን (አላህ) በሙእሚኖች ልብ እንዲወደዱ ያደርጋቸዋል። }[መርየም :6]

በአላህና በአንቺ መካከል ያለውን ግንኙነት አስተካክዩ ፣ምርጥ ለሆኑ ነብያቶች ሚስቶቻቸውን አላህ እንዳስተካከለው ላንቺም ባልሽን አላህ ያስተካክልለሻል። አላህ ስለ ዘከሪያ ሲያወሳ እንዲህ ይላል :-

﴿ فَاسْتَجَبْنَا لَهُ وَوَهَبْنَا لَهُ يَحْيَىٰ وَأَصْلَحْنَا لَهُ زَوْجَهُ ۚ ﴾

[ الأنبياء: 90]

{ለዘከሪያ ልመናውን ተቀበልነው፣የህያ የሚባል ልጅም ሰጠነው፣ ሚስቱንም አስተካከልንለት} [አንቢያእ :90]

ዑመር (رضي الله عنه) እንደተናገሩት :" ሀቅን በመናገር በመፍረድ ኒያው የፀዳ ሰው (በራሱ ላይ እንኳ ቢሆን )፤ በሰውየውና በሰዎች መካከል ያለውን ጉዳይ አላህ ዋስትና ይሰጠዋል። ነገርግን የሌለውን ነገር አለኝ ብሎ እራሱን ያስዋበ አላህ ያዋርደዋል"።

ኢማም አህመድ ሰነድ ጠቅሰው ከዐኢሻ በዘገቡት ሀዲስ :-(አላህ የሚወደውን ስራ ሰርቶ ሰዎችን ያስቆጣ፤ አላህ ከነሱ ያብቃቃዋል(በጊዜ ሂደት ይወዱታል ማለት ነው) ። ነገርግን ሰዎችን ለማስደሰት ብሎ አላህን ካስቆጣ ፤አላህ ወደነሱ ያስጠገዋል።እነሱም ይጠሉታል።

አቡ ነኢም ሂልያ በሚል መፅሀፋቸው እንደጠቀሱት አውን ኢብኑ አብደላህ እንዲህ ይላሉ:-ኡለሞች እርስበርሳቸው 3 ነገር አደራ ይባባሉ ነበር። ይህም :-

1ኛ: አንድን ስራ ለአኺራ ብሎ ከሰራ በዛ ስራ አላህ ዱንያውንም ያብቃቃለታል።

2ኛ :ውስጡን ያሳመረ አላህ ውጪውን ያሳምርለታል።

3ኛ : በአላህና በእሱ መካከል ያለውን ግንኙነት ያሳመረ ሰው ፤ በእሱና በሰዎች መካከል ያለውን አላህ ያስተካክልለታል።

አቡ ሀዚም እንዲህ ይሉ ነበር:- (አንድ ባርያ በእሱና በአላህ መካከል ያለውን ነገር አያሳምርም ፤ አላህ በእሱና በሰዎች መካከል ያለውን ቢያሳምርለት እንጂ ። እንዲሁም በተቃራኒው አንድ ሰው በእሱና በአላህ መካከል ያለውን አያበላሽም ፤ በእሱና በሰዎች መካከል ያለውን አላህ ያበላሸበት ቢሆን እንጂ። ብዙ አካላቶችን ለማስደሰት ከመሞከር አንድን አካል ማስደሰት በጣም ቀላል ነው።አላህን ካስደሰትክ ሁሉም ፊቶች ወደ አንተ ይዞራሉ ።(ሁሉም ይወዱካል)።ነገርግን ከአላህ ጋር ያለህን ግንኙነት ካበላሸክ ሁሉም ይጠሉካል።

ውድ እህቴ ሆይ :- በቀጥተኛ መንገድ ላይ ከፀናሽ ፣በአላህና ባንቺ መካከል ያለውን ካስተካከልሽ ፣ አላህ እንደሚያግዝሽ ና ከመጥፎ ነገር ሁሉ እንደሚጠብቅሽ እርግጠኛ ሁኚ ።ይህ ከውስጥም ከውጪ ሙሉ የሆነ ደስታን ያላብስሻል። አላህ ብሎ ጥሩ፣ አስተዋይ ና ፍትሀዊ ባል ካገባሽ እንኳን ደስ አለሽ ፣ የውስጥም የውጪም ደስታ ታገኛለሽ። ነገር ግን መብቶችሽን በሚያጉድል ባል ብትፈተኚ ውጫዊ ደስታ ባታገኚ እንኳን ውስጣዊ ደስታሽን አታደፍርሽው። የአላህን ውሳኔ በመውደድ ና ትእግስት በማድረግ ውስጣዊ ደስታሽን መገንባት ትችያለሽ።የእውነተኛ ትእግስት አድራጊዎች መገለጫ ይህ ነውና ።ስለ ትእግስት ወደፊት በሌሎች ምእራፎች ላይ እንመለስበታለን ።

ሀያ ምክሮች ለእህቴ ከማግባቷ በፊት በሚል ርእስ በሸይኽ በድር አልዑተይቢ የተፃፈ መፅሀፍ ተተርጉሞ አጠር ባለ መልኩ የቀረበ ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
selehadin nasir jemal Сhanged his profile picture
8 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group