UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

ቀልብ የፅድቅም የጥፋትም የእዝ ማዕከል

~~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~

ጀነት ነፍስ በምትጠላቸው ነገሮች ተከባለች፤ ጀሀነም ደግሞ ነፍስ በምትወዳቸው ሸይጧን በሚያስውባቸው አማላይ ነገሮች፡፡ በብዙ ሁኔታዎቻችን ከአረሕማን ይልቅ ለሸይጧን የቀረብን ነን፡፡ ዐይኖቻችን፣ ጆሮዎቻችን፣ እጆቻችን፣ እግሮቻችን፣ እንዲሁም ምላሳችን ለሸይጧናዊ ተልእኮ የሰሉ ናቸው፡፡ ቀላሉን አምላካዊ ክልከላ መታገስ አቅቶን ከባባድ ሸይጧናዊ ልፋት ላይ እንተጋለን፡፡ ሁሉም የሰውነታችን ክፍሎች ለጥፋት ሲተባበሩ፣ አንዳቸው ብቻ ለሚበቁት ኸይር ግን ተባብረውም ይዝላሉ፡፡ ይሄ ሁሉ የሚሆነው እንግዲህ ማዕከሉን “ዋግ” ሲመታው ነው፡፡ ቀልብ በሺርክ፣ በቢድዐ፣ በስሜት፣ ለሙስሊሞች በምታረግዘው ክፋት፣ … ከተበከለች ታማ፣ ታውካ፣ አመርቅዛ ትሞታለች። ታዲያ ቀልብ ስትሞት ሞቷ ለኸይሩ እንጂ ለሸሩማ ኢንኩቤተር ትሆናለች - ክፉ የሸር መፈልፈያ። ብቻ ሂወቷ በኢማን ካልኩሌተር ሲሰላ ያለ ኢማን ሂወት የለምና ሞታለች - የምር ሞት! ከዚያስ? ከዚያማ ቀልብ ተበላሽታ ሌላው ሰውነት ምን ጤና ሊኖረው? የአካል እንቅስቃሴ በሙሉ ደመ-ነፍሳዊ ይሆናል። ተንቀሳቃሽ ሙት!!! ግድግዳ የተጠጋ እንጨት ሆኖ ሂወት እንዳለው ያስባል፡፡

ከዚህ በኋላ ዐይንም ዐይን ጆሮም ጆሮ አልሆነም፡፡ የሰማያትና የምድር አፈጣጠር፤ የሌሊትና የቀን መተካካት ለሱ ከታክሲዎች መተላፍ፣ ሽንት ቤት ደርሶ ከመመለስ ብዙም ልዩነት የለውም፡፡ ችግሩ ከማዕከሉ ነዋ!

(أَفَلَمۡ یَسِیرُوا۟ فِی ٱلۡأَرۡضِ فَتَكُونَ لَهُمۡ قُلُوبࣱ یَعۡقِلُونَ بِهَاۤ أَوۡ ءَاذَانࣱ یَسۡمَعُونَ بِهَاۖ فَإِنَّهَا لَا تَعۡمَى ٱلۡأَبۡصَـٰرُ وَلَـٰكِن تَعۡمَى ٱلۡقُلُوبُ ٱلَّتِی فِی ٱلصُّدُورِ)

((ለነርሱም በነርሱ የሚያውቁባቸው ልቦች ወይም በነርሱ የሚሰሙባቸው ጆሮዎች ይኖሩዋቸው ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን እነሆ ዐይኖች አይታወሩም። ግን እነዚያ በደረቶች ውስጥ ያሉት ልቦች ይታወራሉ፡፡)) (አልሐጅ፡ 46)

በሌላ በኩል ልብ ከተስተካከለች፣ በኢማን ከተዋበች፣ በተቅዋ ካሸበረቀች መላ ሰውነት ጤና ይኖረዋል፡፡ ፊትም ኑር ይላበሳል፡፡ ዐይኖች በሐራም አይገግሙም፡፡ ጆሮዎች ለሙዚቃ አይቆሙም፡፡ ምላስም የሀሜት ማሽን አትሆንም፡፡ ከውጭ ሙስሊም ያልሆነ ገፅታ እየተስተዋለ ምላስ “ዋናው ልብ ነው” እያለች አታሽቃብጥም፡፡ ማዕከሉ ነቅቶባታላ!

ልብ ስትስተካከል እውነተኛ ማንነት ይገኛል፡፡ ከውስጥም ሙስሊም፣ ከውጭም ሙስሊም! በሐያእ የለሰለሰ፣ በውጭ ገፅታው ያልተኮፈሰ፣ በልቡ የመጠቀ፣ ከእንቶ ፈንቶ የራቀ ልዩ ስብእና!!! አቡበክር አሲዲቅ ረዲየላሁ ዐንሁ ከሌሎች የመጠቁት በሶላትና በፆማቸው ብዛት አልነበረም፡፡ ይልቁንም ልባቸው ውስጥ በፀደቀ ነገር ነበር። ኢማን! የቀልብ ልዩ ክብር!!!

ባጭሩ ጥፋታችንም ልማታችንም ከልብ ጋር የተሳሰረ ነው ማለት ነው፡፡ ታዲያ እኔና እርሶ የቱጋ ነን? ሰገነት ወይስ ጫማ ተራ? ነው ወይስ መሀል ሰፋሪ? በሌላ አነጋገር ልባችን ጤነኛ ነው? በሽተኛ ነው? ወይስ ሙት ነው?

ለካ ይህንንም ለማወቅ ልብ ያስፈልጋል፡፡ ((ባለ ልቦናዎቹ እንጂ አይገነዘቡም)) አይደል ያለው ኻሊቁ?

አንተ ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው ጌታችን ሆይ! ልቦቻችንን ወደ ትእዛዝህ አዙርልን። በዲንህም atsnan 🤲🤲🤲🤲🤲

https://t.me/IbnuMunewor 👈👈👈👈

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Abdullah Nesru Сhanged his profile picture
7 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group