Hayat Abdullahi Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
0
No followings
Translation is not possible.

‹አል-አቅሷ› የመጀመሪያው የሙስሊሞች ቂብላ

1. መስጂድ አል-አቅሷ የቦታና የመስጂድ ሥም ብቻ ሳይሆን ከእስልምና ሃይማኖት ጋር የሚያገናኙት በርካታ ቁምነገሮች አሉ፡፡ አላህ (ሱ.ወ.) መስጂድ አል-አቅሷና ዙሪያውን የተባረከና የተቀደሰ አካበቢ ብሎታል፡፡

(አል-ኢስራእ ፡1)

2. ሌላው አል-አቅሷን ከሙስሊሞች የሚያስተሳስረው የኢስራእና ሚዕራጅ ምድር መሆኑ ነው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ወደ ሰማዩ ዓለም ጉዞ ባደረጉ ጊዜ ከመካው መስጂድ ወደ መስጂድ አልአቅሷ ከዚያም በመነሳት ነበር ወደ ሰማዩ ዓለም የተጓዙት፡፡ ነቢዩ ከመካ ወደ በይት አልመቅዲስ መጓዛቸው የቦታውን ታላቅነትና ቅድስና ያመለክታል፡፡

3. በአል-አቅሷ መስጂድ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ነቢያትን ኢማም ሆነው አሰግደዋል፡፡

4. የነቢያት አባት ነቢዩ ኢብራሂምን (ዐ.ሰ.) ጨምሮ አል-አቅሷና አካባቢው ብዙ የአሏህ ነቢያት የተላኩበት ምድር ነው፡፡

5. እንደ አብዛኞቹ ዑለማኦች ስምምነት አል-አቅሷን ለመጀመሪያ ጊዜ የገነቡት አባታችን አደም (ዐ.ሰ.) ሲሆኑ ኋላ ላይ ግን ነቢዩ ሱለይማን ኢብኑ ነቢዩ ዳዉድ (ዐ.ሰ.) ግንባታውን በማደስ አጠናከሩት፡፡

6. በምድር ላይ አሏህን ለማምለክ ታስቦ የተገነባው የመጀመሪያው መስጂድ መስጂድ አልሐራም (ከዕባ) መሆኑ ይታወቃል፡፡ አል-አቅሷ በምድር ላይ የተገነባ ሁለተኛው መስጂድ ሲሆን በሱ እና በከዕባ መካከል የአርባ አመት ዕድሜ ብቻ ነው ያለው፡፡

7. አል-አቅሷ የመጀመሪያው የሙስሊሞች ቂብላ ነው፡፡ ሙስሊሞች ቂብላ/የሶላት መቀጣጫ/ ወደ ከዕባ/መካ/ እንዲሆነ ከመደረጉ በፊት ለአሥራ ስድስት ወይም ለአሥራ ሰባት ወራት ወደዚያ ዞረው ሰግደዋል፡፡

8. ጓዝ ተጭኖና ስንቅ ተቋጥሮ ለጉብኝትም ሆነ ለሶላት ከሚኬድባቸው ሶስት መስጊዶች ውስጥ አንዱ አል-አቅሷ ነው፡፡

9. በአልአቅሷ ውስጥ የሚሰገድ ሶላት በሌላው መስጂድ ውስጥ ከሚሰገደው በደረጃ በአምስት መቶ እጥፍ ይበልጣል፡፡

10. በአል-አቅሷ መስጂድ ውስጥ የሚሰገደውን ሶላት ሊበልጥ የሚችለው በመካ (መስጂድ አልሐራም)ና በመዲና የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) መስጂድ ውስጥ የሚሰገደው ሶላት ብቻ ነው፡፡

11. አሏህ ሐቅ ላይ ሆነው ለሚዘልቁ በበይት አልመቅዲስ ጉያ ለሚገኙ ሙስሊሞች ድልን ድል እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቷል፡፡

12. በርካታ ሶሓቦችና ትላልቅ ደጋግ ሰዎች የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ስለ አል-አቅሷ ደረጃና ቅድስና ያስተማሩትን በመከተል ወደዚያ ሄደዋል፡፡ ጎብኝተውታል፡፡ ሰግደውበታል፡፡

13. አል-አቅሷ በታሪክ በተለያዩ ገዥዎች ሥር በቅብብሎሽ ከቆየ በኋላ ሙስሊሞች የከፈቱት በኸሊፋ ዑመር ኢብኑ አልኸጣብ (ረ.ዐ.) ዘመን ነበር፡፡

14. ከዚያ በኋላ በርካታ ሶሓቦች በበይት አልመቅዲስ በመገኘት ተምረዋል፣ አስተምረዋል፡፡ እዚያው ቆይተው ከሞቱት ታላላቅ ሶሓቦች መካከል ዑባዳ ኢብኑ አስሷሚት እና ሸዳድ ኢብኑ አውስ (ረ.ዐ.) ይገኙበታል፡፡ የተቀበሩትም ከመስጂዱ ቅጥር ግቢ ውጭ በሚገኘው ባብ አር-ረሕመህ በሚሰኘው ቦታ ላይ ነው፡፡

15. አልአቅሷን ከጎበኙ ታላላቅ ሶሓቦች መካከል ዑመር ኢብኑ አልኸጣብ፣ አቡ ዑበይዳ፣ የምእመናን እናት ሶፍያ ፣ ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል፣ ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር፣ ኻሊድ ኢብኑ አልወሊድ፣ አቡ ዘር፣ አቡ ደርዳእ፣ ሰልማን አልፋሪሲይ፣ ዐምር ኢብኑ አልዓስ፣ ሰዒድ ኢብኑ ዘይድ፣ አቢ ሁረይራ፣ ዐብዱላህ ኢብኑ ዐምር እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

16. በርካታ ትላልቅ የሙስሊሙ ዓለም ሊቃውንትም ለትምህርትና ለኑሮ ወደዚያው ተጉዘዋል፡፡ ታዋቂው ሙፈሲር ሙቃቲል ቢን ሱለይማን፣ ኢማም አልአውዛዒ፣ ኢማም ሱፍያን አስሠውሪይ፣ ኢማም ለይሥ ኢብኑ ሰዕድ፣ ሻፊዒይና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

17. ይህ አካባቢ የሰው ልጆች ከሞት በኋላ የሚነዱትና እንዲሰበሰቡ የሚደረጉበት ምድርም ነው፡፡

18. አል-አቅሷና ምሥራቅ የአል-ቁድስ ከተማን አይሁዶች የተቆጠጣሩት የግማሽ ምዕተ አመት ዕድሜ አንኳን አልሞላውም፡፡

የፍልስጤም ምድርም ሆነ በአጠቃለይ ሻም የሚባለው ሀገር የበርካታ የአሏህ ነቢያት መፍለቂያ ነው፡፡ አል-አቅሷ ደግሞ ሻም የሚባለው ምድር ልብ ነው፡፡

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group