UMMA TOKEN INVESTOR

About me

💝√ልክህ ያልሆነን ይዘህ ሙሉ ከምትሆን፣ልክህን እስከምታገኝ ጎደሎ መሆንህ ውበት አለው።√💝

Translation is not possible.

🕊🕊...ሹራ 28...🕊🕊

💕suman(sumeyra)

<<በማጣት ብቻ የተሞላ አለም ውስጥ መኖር እጅጉን ያደክማል አያቴ>>

አልኳት ከተቀመጠችበት ወንበር ስር እየተቀመጥኩ

<<ዱንያ ባህሪዋ ነው ግን ልጄ ማጣት በራሱ የማግኛ የመጀመሪያው መንገድ ነው!!>>አለቺኝ ፀጉሬን እየደባበሰች

<<ማግኘት እና ማጣት ምን ያያዛቸዋል አያቴ>>

<<እንዴታ ያያዛቸዋል እንጂ ልጄ!!ላንተ በማይበጅህ ወይ በምትወደው ነገር በመነጠቅ አላህ ውዴታውን ገልፆ ከዚያም የሚተካልህ ነገር ከበፊቱ የተሻለ ነው ካንተ ሚጠበቀው ሰብር አድርጎ ኸይርን መከጀል ነው።እንጂ የሚነጥቅህ ሊሰጥህ መሆኑን አትርሳ>>

<<አላህ ከሰብረኞቹ ይጨምረን>>

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ከሰኞ እስከ ጁሙዓ "ድል 🇵🇸ለፈለስጢን" እያለ ይሰነብትና

ቅዳሜ እና እሁድ ሲሆን "ድል ለአርሰናል" ብሎ የሚጮህ ማንነቱን የረሳ የባከነ ስብስብ ይዘን እኮ ነው “የሙስሊሞቹ ድል ዘገየ” የምንለው።

منقول

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

👉ነብያችን - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦

[ በኔ ላይ አንድ ሰለዋትን ያወረደ ሰው፤ አላህ በሱ ላይ አስር ሰለዋትን ያወርድበታል። ] (ሙስሊም ዘግቦታል).

✨✨✨✨

اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አባት ሁለት ሴት ልጆቹን ዳረ። አንዷን ለገበሬ አንዷን ደሞ ለሸክላ ሰሪነበር የዳረው፤ ከአመት በኋላ ሊዘይራቸው ብሎ ከአገር ወጣ። ዚያራውን የቤቱ ታላቅ ከሆነችው ለገበሬው ከዳራት ልጁ ጀመረ፤ እሷም እጅግ በደስታ ተቀበለችው።

"እንዴት ነሽ ኑሮ እንዴት ይዞሻል በምንስ እየኖርሽ ነው" ብሎ ጠየቃት

"ባለቤቴ መሬት ተከራይቶ ነው ያረሰው ፣እህሉን ደግሞ በብድር ነው የወሰደው አሁን ዘርቶታል። ዝናብ እየጠበቅን ነው፤ ከዘነበ ኢንሻአላህ ምርቱ ጥሩ ይሆናል ኑሯችንም ይሻሻላል፤ ካልዘነበ ግን አደጋ ውስጥ ነን።"አለችው

ከዚያም ወደ ሁለተኛ ልጁ አመራ እሷም በደስታ ተቀበለችው።

"ኑሮ እንዴት ነው በምንስ ነው የምትኖሩት"አላት ።

"ባለቤቴ በብድር ነው የሸክላ አፈር የገዛው፤አሁን ብዙ የሸክላ ምርት አዘጋጅቶ መድረቁን እየተጠባበቀ ነው። በየቀኑ ፀሀይ የሚወጣ ከሆነ ምርቱ ይሄድለታል፤በኑሯችን ላይም ለውጥ ይኖራል።የሚዘንብ ከሆነ ግን ሸክላው ይበላሻል።"አለችው

አባት ልጆቹን ከጎበኘ በኋላ ወደ አገሩ ተመለሰ፤ቤቱ ሲደርስ የልጆቹ እናት ስለ ሁኔታቸው ጠየቀችው።እሱም እንዲህ አላት :-

"ከዘነበም አልሃምዱሊላህ በይ ካልዘነበም አልሃምዱሊላህ በይ።"

እንግዲህ የዱንያ ነገር እንዲህ ነው፤ አንዱ የሚፈልገውን ሌላው አይፈልገውም ፤ ላንዱ የሚስማማው ለሌላው አይስማማውም፤ ለአንዱ መሰናክሉ ለሌላው የስኬት መንገዱ ነው። ብናዝንም ብንደሰትም ብናጣም ብናገኝም ቢደላንም ባይደላንም በሁሉም ሁኔታችን ውስጥ አልሃምዱሊላህ አላ ኩሊ ሀል እንበል።አላህ አመስጋኝ ባሮቹን ይወዳልና

አልሃምዱሊላህ♥♥♥

አልሃምዱሊላህ ♥♥♥

አልሃምዱሊላህ ♥♥♥

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ጠራራ ፀሀይ ላይ ከመቃብሮች መሀል ባህሉል የተባለ የከተማው

ዕውቅ እብድ ቁጭ ብሏል። (160 አመተ ሂጅራ)

በግዜው የሙስሊሙን አለም ሲያስተዳድር የነበረው ሀሩነ-ረሺድ

ድንገት ከመቃብር መሀል የተቀመጠውን እብድ ይመለከተዋል።

ንጉስ ሀሩን የማፌዝ ገፅታ እየተነበበበት፦ «አንተ ባህሉል! እንተ

ቆይ መች ነው ሰው ምትሆነው?» ብሎ ጠራው።

ከመቃብሮች መሀል ብድግ አለ። ዙርያውን በአይኑ ቃኘ'ና

ከአጠገቡ ከምትገኝ ዛፍ ላይ በርጋታ ወጥቶ፦ «አንተ ሀሩን! አንተ

ቀውስ! ቆይ ግን መች ይሁን ሰው ምትሆነው?» ብሎ ጮኸበት።

ንጉስ ሀሩን የተቀመጠባትን ፈረስ በዝግታ እየጋለበ መጥቶ ከዛፏ

ስር ቆመ።

እዝያው ፈረሱ ጀርባ ላይ ተንደላቅቆ፦ «እንዴ! እኔ ነኝ እብድ ወይስ

በዚ ጠራራ ፀሀይ መቃብሮች ላይ ምትቀመጠው አንተ ነህ

እብድ?»

«እኔማ ጤነኛ ነኝ» አለ ባህሉል፤ ሙሉ መተማመን ፊቱ ላይ

እየተስተዋለበት።

«እንዴት ሆኖ...?» ሀሩን የማሾፍ ስሜት የተቀላቀለበት ጥያቄ

ጠየቀ።

ባህሉልም ወደ ንጉሱ ቤተ-መንግስት እያመላከተ፦ «ያኛው ጠፊ

እንደሆነ አውቃለሁ። ይኸኛው ደግሞ (መቃብር) ዘውታሪ

እንደሆነም አውቃለሁ።

ስለዚህ እኔ ይኸኛውን ከዝያኛው አስበልጬ ገንብቸዋለሁ። አንተ

ደግሞ እንደሚታወቀው ያኛውን ብቻ ገንብተህ ይኸኛውን

አፍርሰኸዋል።

ምንም እንኳን ከገነባኸው ህንፃ ተነቅለህ ወዳፈረስከው መቃብርህ

ወራጅ እንደሆንክ ብታምንም ግን መሄድን አትሻም» ብሎ በአውላላ

የትካዜ ሜዳ ላይ ንጉሱን አደናገረው።

ባህሉል ንግግሩን ቀጥሏል፦ «ታድያ ከኔ እና ከንተ ማናችን ነን

እብድ መባል ያለብን...»

ካማረው ፈረስ ላይ በክብር ቁጭ ያለው ንጉስ ከጉንጮቹ እንደ

ጅረት የሚፈሰው እንባው ፂሙን አረጠበ።

ንጉስ የሀፍረት ስሜት ውስጥ ሆኖ፦ «ባህሉል ሆይ! ወላሂ አንተ

ትክክል ነህ። እባክህ ትንሽ ምክር ጨምርልኝ» አለው።

«ቁርአን ይበቃኻል፤ ምክሮቹን ጠበቅ አድርገህ ያዝ» አለው

ባህሉል።

«እሺ ምትፈልገውን ንገረኝ'ና ልፈፅምልህ» አለው ንጉስ ከግዛቱ

ሊያስጠቅመው።

«አዎን! 3 ምፈልገው ነገር አለ። ከፈፀምክልኝ አመሰግንሃለሁ»

አለው ባህሉል ከዛፉ ላይ ቁጭ ብሎ።

ንጉስም፦«ጠይቀኝ» አለ፤ ሙሉ መተማመን ፊቱ ላይ እየተነበበ።

ባህሉል፦«እድሜዬን ጨምርልኝ»

ንጉስ፦ «ይኸንን እንኳን አልችልም»

ባህሉል፦ «ከመለከል መውት ጠብቀኝ»

ንጉስ፦ «ኧረ አልችልም»

ባህሉል፦ «እሺ ከእሳት ታድገኸኝ ጀነት አስገባኝ»

ንጉስ፦ «በምን አቅሜ...!»

ባህሉል፦ «አየህ አንተ ባርያ እንጂ ገዢ አይደለህም፤ እኔም ባንተ

የሚፈፀምልኝ ምንም ጉዳይ የለኝም»

منقول✓✓✓

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group