UMMA TOKEN INVESTOR

About me

‏‏ارْحَمْ مَنْ فِي الأَرْضِ يَرْحَمْكَ مَنْ فِي السَّمَاءِ ‏ ‏

Translation is not possible.

በጣም አስተማሪና ድንቅ ግጥም ጨርሳችሁ አንብቡት

.............ማን ይሆን ?...........

ማን ይሆን ከኛ ውስጥ ኸቲማው ያማረ

ሞት የቀለለለት ጉዞው የሰመረ

ለማን ይሆን ምቹ የጨለማው ቤቱ

አላህ የከበበው በሰፊው ራህመቱ

ተነስ ተብሎ ጡሩንባ ሲነፋ

ውስጡዋ ያለን ሁሉ መሬት ስትተፋ

ማን ይሆን ከኛ ውስጥ ትልቅ ባለተስፋ

ባይተዋር የማይሆን መንገድ የማይጠፍ

ማን ሞተ ከኛ ውስጥ በሀጅ ላይ እያለ

ነገን የሚነሳ ለበይክ እያለ

በጅሀድ ማን ሞተ እምነቱን አንግሶ

ነገን የሚወጣ በደም ተለውሶ

እንደ እሳት እራት ሲጨናበስ ኸልቁ

እነማን ይሆኑ በውጤት የላቁ

ክስተቱን ያልፈሩ መውጫውን ያወቁ

በመህሸር ላይ ቆሞ የሰው ልጅ ሲታመስ

ዋ! ነፋሴ እያለ ሁሉም ሰው ሲላቀስ

ማን ይሆን ከኛ ውስጥ ከውስጣችን እያለ

ነገን ማይደነግጥ ጭንቁ የቀለለ

ሰው ጠላቱ ሲሆን የልብ ጓደኛ

አላህ የወደደው ማን ይጠራል ከኛ

ሰው በላቡ ሲጠመቅ በጥም ሲተራመስ

ከነብያችን ሀውድ ማን ይሆን የሚቀምስ

ፀሀይ ስትቀርብ የስንዝር ያህል

ማን ይሆን ከኛ ውስጥ በጥላው የሚውል

ሰው ሁሉ ሲሰለፋ ለምርመራ ሲቀርብ

ውጤቱን ለማወቅ ሲጨነቅ ሲጠበብ

ከኛ ውስጥ ኪታቡን ማን ከቀኝ ያገኛል

እዩልኝ እያለ ሰዎች ይጋብዛል

ሰው ሁሉ ጎድሎበት በዕዳ ሲፈላለግ

ከወላጅ ከሚስቱ ከልጁ ሲደበቅ

የኸይር ሚዛኑ ማነው የሚደፍ

ደስታው ልክ ያለፈ ሀሴቱ የሰፍ

ኧረ ማነው ከኛ አላህን የፈራ

መልካሞች ጋር ነገን የሚጠራ

ማን አለ ከኛ ውስጥ በሚስጥር የሰራ

በለሊት ተነስቶ እንባውን የዘራ

ከፈጣሪው ጋራ በሚስጥር ያወራ

ፊቶች ሲጨልሙ ፊቱ የሚያበራ

ማን ይሆን ከኛ ውስጥ የሸፉዓ ብቁ

መሄጃ ጠፍቶዋቸው ሰዎች ሲጨነቁ

ማንን ያናግራል አላህ ጠጋ ብሎ

ከሰው ሁሉ መርጦ ከህዝቦች ነጥሎ

ሰው ሁሉ ሲዋረድ በፋርዱ አደባባይ

ማነው ከኛ መሀል በዙፋን የሚታይ

ከኛ መሀል ማነው ህልሙ የሚሳካ

የፈጣሪውን ፊት አይቶ የሚረካ

ማነው ከኛ መሀል በስም የሚጠራ

ከእናት ከአባቱ ከሚወደው ጋራ

እነማን ይሆኑ ነገን የሚያዩ

ሰዎች በስራቸው ደረጃ ሲለዩ

ከሰባ ሶስቱ /73/ ሰልፍ አንዱ የጀነት ሲሆን

ማነው ከኛ መሀል ከአንዱ የሚሆን

የእኔ እና እናንተ ምን ይሆን እጣችን

ከየትኛው አንጃ ይሆን ምድባችን

ማነው ከኛ መሀል በእርግጥ ያልታደለ

የአላህ ራህመት ሰፊ ሆኖ ሳለ

ከጀሀነም እሳት ይግባ የተባለ

ጀሀነም ስትራብ ሰው ስታነፈንፍ

ያዳለጠው ሲወድቅ ትረፍ ያለው ሲተርፍ

ማን ይሆን ሲራጡን የሚያልፈው በሮ

የእሳቱን ጉድጓድ ወደኋላ ጥሎ

ሰው ሳቅ በሳቅ ሆነ ዋለ ሲፈነድቅ

ለረጅሙ ጉዞ ትንሽም ሳይሰንቅ

እንዴት ዋልክ ሲሉት ሰው ደህና ነኝ እያለ

ቀብር የሚባለው ከፊቱ እያለ

እንደምን ነህ ሲሉት ሰው ሰላም ነኝ እያለ

ሲራጥ ሳይታለፍ የምን ሰላም አለ

ሲራጥ ሳይታለፍ የምን ሰላም አለ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

#ሀቅ ሀቅነቱን ሊቀይር አይችልም ትላንት ሀቅ የነበረ ነገር ዛሬ ባጢል ሊሆን አይችልም

‌‏قال شيخ الإسلام محمد بن عبد الوهاب (١٢٠٦هـ) رحمه الله

🥀ታላቁ ሙጀዲድ ሙሀመድ ኢብኑ አብድል ወሓብ እደዚህ ብለዋል

الباطل لا يصير حقا بعظمة قائله وجلالته

ባጢል መቼም ሀቅ ሊሆን አይችልም ተናጋሪው ምንም ትልቅ እልቅና ያለው ቢሆንም [الجواهر المضية ص ٢٢]

https://t.me/Atharnsa143

Telegram: Contact @Atharnsa143

Telegram: Contact @Atharnsa143

✍️ ይህ በአላህ ፍቃድ አጫጭር ሀዲሶች, እንዲሁም ጣፋጭና ጠቃሚ የሆኑ የሰለፎቻችን አሳሮች ወርቃማ ንግግሮችና አጫጭር የኦለሞችን ንግግር ከትርጉም ጋር የሚለቀቅበት ቻናል ነው። ⤴️ ይህንን ቻናል ለወዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ የኽይር ስራ ተካፋይ ይሁኑ። ? ቻናሉን ለማግኘት ⤵️⤵️⤵️ ? https://t.me/Atharnsa143
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

#ጥሩ ስነምግባር #ማለት

‏قال الإمام ابن المبارك -رحمه الله

‏حسن الخلق طلاقة الوجه وبذل المعروف ‏وكف الأذى وأن تحتمل ما يكون من الناس

#ጥሩ ስነምግባር ማለት የፊት #ፈገግታ ጥሩን ነገር ለሰዎች ማድረግ መስጠት ሰዎችን አዛ አለማድረግ አለመበደል ከሰዎች አዛ በሚደርስብህ ጊዜ መቻል መታገስ ማለት ነው

ይኸ ነው ጥሩ ስነምግባር አሉ አላህ ያላብሰንና !!

#ምንጭ

جامع العلوم والحكم ١٦٠

https://t.me/Atharnsa143

Telegram: Contact @Atharnsa143

Telegram: Contact @Atharnsa143

✍️ ይህ በአላህ ፍቃድ አጫጭር ሀዲሶች, እንዲሁም ጣፋጭና ጠቃሚ የሆኑ የሰለፎቻችን አሳሮች ወርቃማ ንግግሮችና አጫጭር የኦለሞችን ንግግር ከትርጉም ጋር የሚለቀቅበት ቻናል ነው። ⤴️ ይህንን ቻናል ለወዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ የኽይር ስራ ተካፋይ ይሁኑ። ? ቻናሉን ለማግኘት ⤵️⤵️⤵️ ? https://t.me/Atharnsa143
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ዱኒያ የአማኞች እስር ቤት የካሃድዎች ጀነት ነች

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

قال رسول الله صلى الله عليه وسلم

سلوا الله من علم نافعا، وتعوزو بالله من علم لاينفع

#የአላህ መልክተኛ ረሱል ሰለላህ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ

#አላህን ጠቃሚ እውቀትን #ጠይቁት ከማይጠቅም እውቀትም በአላህ ተጠበቁ

#ምንጭ

{السلسلة الصحيحة ١٥١١}

Send as a message
Share on my page
Share in the group