Translation is not possible.
➡️ ተውሒድ 1 ያደርጋል
በምስራቅ በምዕራብ በሰሜን ያላቹህ
እንዲሁም በደቡብ በውጭም ያላቹህ
ሙስሊም ሙስሊማቶች እንደ'ምን አላቹህ
የአላህ ሰላም  እዝነት ሁሌ አይለያቹህ
አደራ እወቁልን አንደምወዳቹህ
በያላቹህበት አላህ ይጠበቃቹህ
በውል ተገንዝበን  የጠላትን ሴራ
አፋርና  ትግራይ   ኦሮሞና  አማራ
ወላይታና  ጋሞ   ባንድ   ብንጣራ
ሃበሻ  እንዲፈካ  የተውሂዱ ጮራ
ጨለማው ተገፎ ሱናው እንዲያበራ
አቤት  ውበታችን   ስንቆም  በጋራ
ሲዳማ ሶማሌ  ጉራጌ ወላይታ
ሐረሪ ጌዴኦ ከፋ ጉሙዝ ቤርታ
ሀዲያና ጋሞ     ኮንሶና ከንባታ
ብሄር ሳይገድበን ወሬና አሉባልታ
መስራት ያስፈልጋል በቀንም በማታ
ተውሒድን ለማድረስ በየሁሉም ቦታ
ሽርክ ተንሰራፍቷል ከተማ እስከ ገጠር
ድሬዳዋም በለው አዲስ አባ ሸገር
መቀሌና አሶሳ   ቤንሻንጉል ሀረር
ሰመራና አሳይታ ዲላ ካብሪ ዳሃር
ጅግጅጋና ጅንካ ሽሬ  ደብረ ታቦር
ደሴና ወልዲያ እንዲሁም ባህርዳር
ብዙ ኮተት አለ አዲስ ዘመን ጎንደር
ነቀምት ሻሸመኔ  ቢሾፍቱና አሰላ
ዶሎ ኦዶ ሀረሪ ናዝሬትም ጋንቤላ
መወገድ ያለበት አለ  ብዙ  አተላ
ወላይታና አርባ ምንጭ  ሀዋሳና ጅማ
ደብረ ማርቆስ አድዋ አክሱምና አዳማ
ብዙ ፍጥረት አለ ተውሒድን ያልተሰማ
አዎ!
ሽርክን አንኮታክቶ ተውሒድን ለማድረስ
ቢድዓን በታትኖ  ሱናችን  ለማንገስ
እንጣር እንትጋ እስክትወጣ እስትንፋስ
ኩፍር ይከፋፍላል ኢስላም ያዛምዳል
ሽርክ ይለያየናል  ተውሒድ ያጣምራል
ቢድዓ  ይበትናል    ሱና ያስተሳስራል
ቢመርህም ዋጠው ተውሒድ 1 ያደርጋል
✍Abu Imran
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/Abu_lmran_Alaseriy/3502
🌸💐Join & Share 💐🌸👇
https://t.me/Nasiha4all/928
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group