የኢራን ወታደራዊ አመራሮች የአሜሪካው የባህር ኃይል ወደ ፋርስ ባህረ ሰላጤ እየተጠጋ መሆኑን ተከትሎ እጅግ ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።
ኢራን ትኩረት ያደረገችው በአሁኑ ወቅት ወደ ቀጠናው እየገሰገሰች ባለው የአሜሪካዋ ግዙፍ የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ "USS Abraham Lincoln" ላይ ሲሆን መርከቧን ለማጥፋት ዘመናዊ የሆኑትንና ለመመከት እጅግ አስቸጋሪ የተባሉትን "ሃይፐር ሶኒክ" ሚሳኤሎቿን እንደምትጠቀም አስታውቃለች።
የአሜሪካ ባህር ኃይል የኢራንን የባህር ዳርቻ አልፎ ወደ ውስጥ "ጎጆ" ለመግባት ከሞከረ መርከቧና አጃቢዎቿ የኢራን ሚሳኤሎች ሲሳይ እንደሚሆኑ ቴህራን ዝታለች።