Translation is not possible.

«በትምህርት ቤቶች በየጊዜው የሚያገረሸው የኒቃብ ክልከላ ጉዳይ ቋሚ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል።

ፊትን ከባዕድ ወንዶች መሸፈን ግዴታ መሆኑ የአብዛኛዎቹ ዑለማዎች አቋም ነው።

ሆኖም ሴቶች ፊትና በማይሰጋበት ሁኔታ ለአስፈላጊ ጉዳይ ፊታቸውን ለወንዶች ማሳየት  እንደሚችሉ የሁሉም የፊቅህ ሊቃውንት ንግግር ያሳያል።

በዚህ መሰረት ተማሪዋ ወደ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ስትገባ፣ ወደ ፈተና ማእድ ስትገባ፣  አጠራጣሪ ሁኔታ ሲኖር ወይም በማንኛውም ጊዜ ማንነቷን ማጣራትና ከመታወቂያዋ ጋር ማመሳከር ሲያሰፈልግ ፊቷን ገልጣ አሳይታ መልሳ መሸፈን ትችላለች።

«ሙሉ በሙሉ ተገልጠሽ ካልቆየሽ አትገቢም!» ማለት ግን ሀይማኖታዊ መብትን በግልፅ የሚጋፋ፣ ሴኪዩላሪዝም ራሱ የማይደግፈው… ምንም አግባብነት የሌለው የግለሰቦች ድርቅና ነው።»

#ሒጃብ #ኒቃብ #ትምህርት

#ሀገራዊ_ምክክር

✍ ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group