Translation is not possible.
كن قويا /ጠንካራ ሁን/
ወዳጄ ሆይ ! በዚህ ዱንያ ላይ ጠንካራ ሁን ህይወት ደካሞችን አትቀበልም።
— ወዳንተ ከሚመጣው አውሎ ንፋስ ጠንካራ ሁን !!
— ጠንካራ ሁን ከተደቀነብህ ፈተና
— ጠንካራ ሁን በተለያዩ ጉዳዮችህ ላይ
★ ዘመናት ይፈትኑሀል ወደሞኞች ስትሄድ ታያለህ ግን ጠንካራ ሁን ህይወት ደካሞችን አትቀበልም።
★ ምናልባት ትሠደዳለህ ከሀገርህ ትርቃለህ የእናትህ ቂጣ ዳግም ትናፍቃለህ ግን ብርቱ ሁን ህይወት ደካሞችን አትቀበልም። በለው ያ ሞትና ውድቀትህን ለሚጠባበቀው ከፈኔን አታዘጋጅልኝ እኔ አልሞትኩም ገና ጡንቻዬ መሬት መንቀጥቀጥንና መብረቅን ያስተናግዳል። ጠንካራ ሁን ህይወት ደካሞችን አትቀበልም
★ በፈተናዎችና በብርቱ ጉዳዮች ፊት ጠንካራ ሁን አንድን ነገር አልመህ እውነታው ግን ሌላ ይሆንብሀል ግን ብርቱ ሁን።
★አይንህ ውስጥ የገባች ትንሽ ነገር ልታጠፋህ ስትል ትመለከታለህ ግን ጠንካራ ሁን።
★ ዱንያ ላይ ራስህን ብቸኛ አድርገህ ታገኛለህ ያለ ወዳጅ ያለ ጓደኛ ያለ ወንድም
የዱንያን መከራ ብቻህን ትጋደላለህ ግን አስታውስ ዱንያ ምንም ብትሆን አበደን ለደካሞች ቦታ የላትም።
የአላህን ቃል አስታውስ
" በጌታህ ፍርድ ታገስ ! አንተ በጥበቃችን ስር ነህና"
የትርጉም ፅሁፍ
ሉሊ የሰርግ ግጥሞች
Send as a message
Share on my page
Share in the group