እስራኤላውያን ሰፋሪዎች በአል-አቅሳ መስጊድ ግቢ ውስጥ ወረራ ፈፀሙ
የፍልስጤም የዜና ወኪል ዋፋ እንደዘገበው እስራኤላውያን ሰፋሪዎች በእስራኤል የፖሊስ መኮንኖች ጥበቃ ስር ሶስተኛውን ቅዱስ ስፍራ አል- አቅሳ ላይ ወረራ መፈፀማቸው ይታወሳል።
በአይሁድ ህግ መሰረት ወደ ግቢው ማንኛውም ክፍል መግባት ለአይሁዶች የተከለከለ ቢሆንም በየጊዜው የሚከሰት አጋጣሚ ነው። የእስራኤል ባለስልጣናት ከጥቅምት 7 ጀምሮ ፍልስጤማውያንን ለዓርብ ፀሎት ወደ ስፍራው እንዳይገቡ ደጋግመው ከልክለዋል ፣ይህም ብዙዎች በብሉይ ከተማ አቅራቢያ ባሉ ጎዳናዎች ላይ እንዲጸልዩ አስገድዳቸዋል ። የእስራኤል ወታደሮች በመስጊዱ ውስጥ በሚገኙ ፍልስጤማውያን ምእመናን ላይ ጥቃት ፈጽመዋል።
በቀጠለው ውጊያ እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ በኩል በሂዝቦላ የሚደርሰውን መጠነ ሰፊ የሮኬት እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ለመመከት የቅድመ መከላከል እርምጃ ወስዳለች። የእስራኤል ጦር እንዳስታወቀው በሺዎች የሚቆጠሩ በኢራን የሚደገፈው የታጠቀ ቡድን የሮኬት ማስወንጨፊያዎችን እሁድ ጠዋት ማውደሙን አስታውቋል። ሂዝቦላህ እና አጋሮቹ ሶስት ተዋጊዎቻቸው መገደላቸውን ተናግረዋል።
ሄዝቦላህ ለተገደለበት ከፍተኛ አዛዥ የበቀል እርምጃ አሁንም መቀጠሉን በመግለፅ 320 ሮኬቶች እና ድሮኖች በእስራኤል ላይ መተኮሱን አስታውቋል። የእስራኤል ጦር እንደገለጸው አንድ የእስራኤል የባህር ኃይል ወታደር በሄዝቦላህ ጥቃት ተገድሏል ብሏል። ዩናይትድ ስቴትስ ከ10 ወራት በላይ የዘለቀው ጦርነት የከፋ ውጊያ ውስጥ እንዳይገባ እየሰራሁ ነው ስትል አስታውቃለች።
በጥቅምት 7 በእስራኤል እና በሃማስ መካከል በጋዛ ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በእስራኤል እና በሊባኖስ ድንበር ላይ በየቀኑ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ ይገኛል። በካይሮ በዩናይትድ ስቴትስ የሚደገፈው የጋዛ የሰላም ድርድር የመጨረሻው ዙር ምንም ውጤት አላመጣም። ሃማስ ወደ ድርድሩ ከመሄዱ በፊት አዲስ የእስራኤልን ቅድመ ሁኔታዎች ውድቅ በማድረግ እስራኤል የገባችውን ቃል ሳትፈፅም ቀርታለች ሲል ከሷል። እስራኤል በሀምሌ ወር መጀመሪያ ላይ ከመጨረሻው የውይይት ዙር በኋላ ጥያቄዎቿን ቀይራለች መባሉን አስተባብላለች።
#gaza #palestine #freepalestine #quran