Translation is not possible.

የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ነበር የIT አስተማሪያችን ለምን እንደሆነ በኋላም ባልገባን ምክንያት ሶሻል ሚዲያ አካውንት ያስከፈተን ፤ ፌስቡክም አንዱ ነበር ። ሁላችሁም friend request ወደኔ ላኩ ብሎን ሲያበቃ የምቀበላችሁ ሙሉ profile ያለውን ነው ብሎ ኮራብን ፤ አለፍ ሲልም ከሱ በላይ friend ያገኘ ሰው (አይኖርም እንጂ እያለን😁) በፈለገ ሰአት ከክላስ እንዲወጣ በኔ ክፍለጊዜ እፈቅድለታለሁ ብሎ የFacbookን ደረጃ አልቆ አሳየን😁። ህዝቤ ይሰራራው ጀመር Facbook profile ላይ ምርጥዬ ሆኖ ለመታየት የሚያደርጋቸው ጥረቶችና ሽርጉዶች በአካል የማንተዋወቀው ሌላ ተጨማሪ ሰው ሰው ሆኖብን ከአንድ ሰው ጋር ለመግባባት ሁለቴ ማሰብና ሁለት ቦታ ላይ ሁለት ሰው ሆኖ መገኘት አስፈላጊ ሆነ ። ብቻ በእኔ ስልክ ላይ ብዙ የlogin አገልግሎት በቅልጥፍና እሰጥ ስለነበር ክፍያው የኔን request accept ማድረግ ነበርና በጥቂት ጊዜ አስተማሪውን በለጥኩት ። ምንም እንኳን በአካል መሬት ላይ የምንግባባና እስከነ ኮተታችን የምንተዋወቅ ቢሆንም ፕሮፋይል ላይ በልጦ ለመገኘት እንደማይተዋወቅ ሰው መሸማጠጥ ተጀምሮ ነበር ፤ ዩኒፎርሙን አውልቆ ከክላስ ፎርፎ ትምህርት ቤት ውስጥ የተገኘች መኪና ተደግፎ በጓደኛው ስልክ ፎቶ ተነሳና « ፍቅር ወይስ ገንዘብ ፤ ሲኖርህ ነው ሰው የሚኖርህ » ብሎ ፖሰተ ። ልክ ክላስ ተመልሶ ሲመጣ ዩኒፎርሙን ለብሶ ፣ ስልኩን አመስግኖ መልሶ ፣ የቀጣዩ ክፍለጊዜ አስተማሪ የሰጠውን homework ለመገልበጥ ሲንከላወስ ላየው ግን such is life ያስብላል ። እና እቺን ነገር ያስታወሰኝ even after a decade አየሩ የማይሰምጥ ተመሳሳይ መሆኑ ነው በዚህ ጉዳይ ላይ ፤ እንደውም ብሶበታል እንጂ ። የከፋው ደሞ ለማሳቅ ብሎ ዲን ላይ የሚቀልድ አለ ፤ ሰዎች የእውነት ልባቸው ታፍኖ እዚህ መንደር አዳልጧቸው ተንፈስ ያሉበት ፖስት ስር ሄዶ የሚያስለቅሳቸው አለ ፤ ደሞ😂 ትዳር😂 ፍለጋ😂 የሚመጣና😂 ጥሩ😂 አጋር😂 ለመምሰል😂 የሚጋጋጡም አሉ😂 ፤ እንኳን የረገጠው ቦታ ሁሉ እንኳን ቤተሰቡ ላይ ራሱ ላይ ተፅዕኖ ሳያሳድር እዚህ መቶ አነቃቂ የሚሆንም አለ(የተነቃነቀው ህይወትህን ጠበቅ ብታረግ አይሻልህም) ፤ አረ ብቻ ብዙ ነው ራሴን እንኳን የታዘብኩት ። እና የሚመስለኝ ድስት ግጣሙን አያጣም በሚለው የመጣልህን ሳይሆን የገጠመልህ ላይ ብቻ የእውነት ሁን ፤ አንዳንዱ ትልቅ ድስት ይሆንና እንደ አብዛኛው ድግስ በአመት አንዴ ነው ለቁምነገር የሚበቃው ፤ አንዳንዱ ደሞ ትንሽዬ ይሆንና ነጋ ጠባ ማሞቂያ በመሆኑ የሚለኮስ እሳት ላይ የማታጣው ይሆናል ።እንደምታየው ሳይሆን እንደሚታይህ መሆን የተሻለ ነው ። ደሞስ ምን አስጨነቀህ ለማይኖረው አለም አንተን ስላሳየህ በቀን በማታ ራሱ ሲቃዥ ይኑር እንጂ ። አላህዬ ደጉ ስራህ ትክክል ወይ ሰትረን ወይ የእውነት ሰው አርገን ፤ امين 🤲

የግርጌ ማስታወሻ - በእውነቱ እዚሁ መንደር የሰው ልኮችም አሉና እነሱን ያብዛልን ምኞቴ ነው ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group