Translation is not possible.

ነቢዩ ﷺ ላይ የመዋሸት መዘዝ

🔅ነቢዩ ﷺ ላይ መዋሸት ማለት እሳቸው ያላሉትን ብለዋል ወይም ያላደረጉትን አድርገዋል ማለት ሲሆን ይህ ከከባባድ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው።

ከመሆኑም ጋር በዚህ የሶሸል ሚዲያ ማዕበል በፈነዳበትና ንግዱም በተጧጧፈበት ዘመን ይህን ከባድ ወንጀል ብዙ ሰዎች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ሲዳፈሩትና ነቢዩ ﷺ ያላሉትን ብለዋል፤ ያላደረጉትንም አድርገዋል ሲሉ እንሰማለን።

እነሆ ይህ ድርጊት ወደ ጀሀነም የሚውሰድ መንገድ በመሆኑ የኣኺራህ ጉዳይ የሚያሳስበው በሙሉ ከዚህ እኩይ ተግባር ሊቆጠብና ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል ወይም አድርገዋል ከማለቱ በፊት ቆም ብሎ ሊያስብና ከርሳቸው ጋር አያይዞ ሊናገረው ያሰበው ነገር እውነትና ትክክል መሆኑን ቀድሞ ሊያረጋግጥ እርግጠኛ ካልሆነ ዝምም ሊል ይገባል።

ይህ ካልሆነ ግን እርግጠኛ ያልሆነበትን ነገር ነቢዩ ﷺ ላይ እየቀጠፈና እየለጠፈ የሚናገር ሰው ነገ ጀሀነም ይገባል!

🔅ሩኅሩህና መካሪ ነቢያችን ﷺ በዚህ ዙሪያ ሲናገሩና ሲያስጠነቅቁ የሚከተለውን ብለዋል፥

\"የቅጥፈት ሁሉ ቅጥፈት እኔ ያላልኩትን ብሏል ብሎ መናገር፤ በህልም ያላዩትን አይቻለሁ ማለትና ወላጁ ያልሆነን ሰው ወላጄ ነው ብሎ መናገር ነው \" ብለዋል።

አል-ቡኻሪ ሐ/3509፣ ሙስነድ አሽሻፊዒ ሐ/1213 ላይ ዘግበውታል።

\"እኔ ላይ አትዋሹ! እኔ ላይ የሚዋሽ እሳት ይገባል! \" ሙስሊም ሙቀዲመህ ላይ ዘግበውታል።

\"እኔ ላይ የሚዋሽ ሰው ጀሀነም ውስጥ ቤት ይሰራለታል\" ሙስነድ አሕመድ ሐ/4742፣ ሙስነድ አሽሻፊዒ ሐ/1215 ላይ ዘግበውታል።

💥 በእውቀት ማነስ ወይም ሆነ ብሎ ለርካሽ አላማ፤ እንዲሁም በድፍረትና በግዴለሽነት አላህና መልዕክተኛው ላይ ከመዋሸትና ከሚያስከትለውም መዘዝ አላህ ራሱ ይጠብቀን!

✍ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

ዛዱል-መዓድ

https://telegram.me/ahmedadem

Telegram: Contact @ahmedadem

Telegram: Contact @ahmedadem

በኡስታዝ አሕመድ ኣደም የሚዘጋጁ ተከታታይ ቋሚ ትምህርቶች፣ ፈትዋዎች፣ ሙሓደራዎችና አጫጭር ምክሮች የሚቀርቡበት ቻናል القناة التعليمية الرسمية لأبي عبد الله أحمد بن آدم الشراري دروس في القرآن والعقيدة والفقه وفتاوى ومقالات متنوعة باللغة الأمهرية http://www.youtube.com/c/ZadulMaad
Send as a message
Share on my page
Share in the group