Translation is not possible.

የቱርክ ቀይ ጨረቃ ማህበር ወደ ጋዛ ገብቶ በረሀብ የተጎዱ ፍልስጤማዊያንን እየመገበ ይገኛል።

በዚህም መሰረት የምገባ ዘመቻውን በማስፋት በአሁኑ ሰአት የቱርክ የቀይ ጨረቃ ማህበር በየቀኑ 15,000 ጋዛዊያንን እየመገበ ይገኛል ።

ማህበሩ የተደራሽነት አቅሙን ለማስፋፋት እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ቱርክ ወደ ጋዛ የምታጓጉዘዘውን እርዳታ አጠናክራ ቀጥላለች።

ከ 13 በላይ እርዳታ የያዙ መርከቦችንና በርካታ የአይሮፕላን በረራዎችን ለጋዛ ነዋሪዎች ያጓጓዘቺው ቱርክ በረሀብ ለሚሰቃየው የጋዛ ህዝብ ማስታገሻ ሆናለች።

በርካታ ህፃናት በረሀብ ለመሞት እያጣጣሩ ባሉባት ጋዛ የምግብ እርዳታ በእጅጉ አስፈላጊ ነው። የቱርክ ቀይ ጨረቃ ማህበር ዛሬ በሰጠው መግለጫም \" ከፍልስጤማውያን ወንድሞቻችን ጎን እስከመጨረሻው እንቆማለን \" ብሏል።

መረጃው የ Daily Sabah ነው።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group