Translation is not possible.

📩 መልዕክት ⤵️⤵️⤵️

🚘 ለዐረፋ በዓል ወደ ክፍለ ሀገር ተጓዦች።

🤝 السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

🔖 አል-ፉርቃን ኢስላማዊ ስቱዲዮ እንኳን የ1445 ዓመተ ሂጅራ የዙልሒጃ የመጀመሪያ አስሩ ቀናቶች በሰላም አደረሳችሁ በማለት በተለያዩ የዒባዳ አይነቶች እንድትጠናከሩ ለማስታወስ ይወዳል።

💥 በመቀጠል አመት በዓሉን አስመልክቶ ለዚያራና ቤተሰብ ጥየቃ ወደ ተለያየ ቦታ እና ክፍለ-ሀገር የምትጓዙ ወንድምና እህቶች በሙሉ ስንጓዝ ሸሪዐን በጠበቀ መልኩ ሊሆን ይገባል። ወደ ቤተሰብ በምንጓዝበት ጊዜ ዓላማችን መብላትንና መጠጣት ላይ ብቻ ትኩረት ልናደርግ አይገባም።

💥 ስለዚህ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ትክክለኛውን እስልምና በሰለፎች ግንዛቤ ላልደረሳቸው ማህበረሰቦች የማድረስ ግዴታ ይጠበቅብናል።

💥 በመሆኑም የተለያዩ አጫጭርና ጠቃሚ የሆኑ ሪሳላዎች ማስቀራት የምንችል ኪታቦቹን በመያዝ ማህበረሰባችንን ልናስገነዝብ ይገባል።

💥 ይህንን ማድረግ የማንችል ከሆነ አልፉርቃን ኢስላማዊ ስቱዲዮ እንደተለመደው ወቅቱን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ኡስታዞቻችን ደርሶች ሙሀደራዎችንና እንዲሁም የተለያዩ ዲናዊ ትምህርቶችን በሚሞሪና በፍላሽ አዘጋጅቶ የሚጠብቃችሁ መሆኑን ሲያበስር በታላቅ ደስታ ነው።

📮 ማሳሰብያ በራሳቸው ሚሞሪም ይሁን ፍላሽ በፈለጉት አይነትና መጠን ሲያስጭኑ ምንም አይነት ክፍያ የሌለው መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን።

{ምንም እንኳን በራሳችን መጣራትንና ማድረስ ባንችል በሌሎች ወንድሞች በኩል እንዲደርስ ሰበብ ሆነን የአጅሩ ተካፋይ እንሁን!}

🕌 አድራሻ አዲስ አበባ አለም-ባንክ ከፉርቃን መስጂድ ጎን ለጎን እንገኛለን።

💻 አልፉርቃን ኢስላማዊ ስቱዲዮ

የሰለፊዮች ልሳን!⤵️

📎 https://telegram.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/1660

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group