7 month Translate
Translation is not possible.

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ከጦርነቱ መጠናቀቅ በኋላ ለጋዛ ሰርጥ የተዘጋጀ ዕቅድ ካላወጡ ስልጣን እንደሚለቁ የጦር ካቢኔ ሚኒስትር ቤኒ ጋንትዝ ዝተዋል።

ጋንትዝ በጋዛ የሐማስ አገዛዝን ማብቃትን እና ለግዛቱ ዓለም አቀፍ ሲቪል አስተዳደር መመስረትን ጨምሮ ስድስት “ስትራቴጂካዊ ግቦችን” ለማሳካት የሚያስችለው ዕቅድ እስከ ሰኔ 8 እንዲዘጋጅ ቀነ-ገደብ አስቀምጠዋል።

“አገራዊውን ከግል ጥቅም በላይ ብታስቀምጡ እኛን የመሰሉ የትግል አጋሮች ታገኛላችሁ። ነገር ግን የአክራሪዎችን መንገድ መርጣችሁ መላውን ህዝብ ወደ ገደል ከመራችሁ ካቢኔውን ለመልቀቅ እንገደዳለን” ብለዋል።

ኔታንያሁ አስተያየቱን “ለእስራኤልን ሽንፈት ማለት ነው” ሲሉ አጣጥለውታል።

አለመግባባቱ እየጨመረ የመጣው በጋዛ ሰርጥ በሁለቱም ጫፎች ላይ ውጊያ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ነው። የእስራኤል ወታደሮች በደቡባዊ ራፋህ ከተማ እና የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች በብዛት በሚገኙባት እና የእስራኤል ጦር ከዚህ በፊት የሐማስ ተዋጊዎች እንደሌሉ በተናገሩባት በሰሜናዊቷ የጃባሊያ ከተማ ውጊያው እየተካሄደ ነው።

ሌላኛው የጦር ካቢኔ አባል የመከላከያ ሚኒስትሩ ዮአቭ ጋላንትም ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እስራኤል በጋዛ የሲቪል ሆነ ወታደራዊ አገዛዝን የመቆጣጠር ዕቅድ እንደሌላት በይፋ መናገራቸው ይታወሳል።

https://bbc.in/3yqSSXk

ከጦርነቱ መጠናቀቅ በኋላ ለጋዛ የተዘጋጀ ዕቅድ ከሌለ ከኃላፊነት እንደሚለቁ የእስራኤል ጦርነት ካቢኔ ሚኒስትር ገለጹ - BBC News አማርኛ

ከጦርነቱ መጠናቀቅ በኋላ ለጋዛ የተዘጋጀ ዕቅድ ከሌለ ከኃላፊነት እንደሚለቁ የእስራኤል ጦርነት ካቢኔ ሚኒስትር ገለጹ - BBC News አማርኛ

ጋንትዝ ቅዳሜ ዕለት በቴሌቭዥን ቀርበው ባደረጉት ንግግር የእስራኤል ህዝብ እርስዎን እየተከታተሉ ነው ሲሉ መልእክታቸውን ለኔታንያሁ አስተላልፈዋል።
Send as a message
Share on my page
Share in the group