Translation is not possible.

ምቀኛ ሰው ሲበዛ የሚገርም ፍጡር ነው ። ከራሱ ማግኘት ይልቅ የሚያሳስበው የጓደኛው ማጣት ነው። ወንድምህን አላህ በሆነ መልኩ ፀጋውን ከዋለለት በኋላ በዚያ ላይ ቂም ማርገዝ ፣ በክፋት መመልከት የሰጪውን ጌታ ውሳኔ በይሁንታ አለመቀበል ነው ።

ምቀኝነት ከአማኝ የማይጠበቅ ቆሻሻ ባህሪ ነው ። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ ፡-

لا يجتمعان في جوف عبدٍ الإيمان والحسد

“በአንድ አማኝ ባሪያ ልብ ውስጥ ኢማን እና ምቀኝነት ባንድ ላይ አይሰባሰቡም!” [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 7616]

ከወንድም ጋር ተካፍሎ የበሉት ይጣፍጣል ፣ አብሮ የተጓዙት የጨለማ መንገድ የብርታት ይሆናል ፣ ለወንድም ብለህ ባደረከው ዱዐ ምላሽ የመላኢካዎቹ ይጠብቅሀል ፤ እኩል በተዘረጋልህ መሬት ላይ የገጠሙህን ዳገትና ቁልቁለት በርትተህ ተወጣቸው እንጂ ታግሎ የወጣውን ጎትተህ አትጣለው ። አላህ መልካም ጓደኛን ይስጠን ፤ امين

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group