Хьо дакъа дацанаш махь йоьтта.

🤝እንኳን አደረሳችሁ‼️

       ማለት አይቻልምን❓❓

✍የትኛውንም "እስልምናን አቃለሁ" የሚል ሙስሊም “ከእስልምና ውጪ ያሉ እምነቶች የባጢል እምነቶች ናቸው” ብሎ ያምናል።

✍የትኛውንም "ክርስትናን አቃለሁ" የሚል ክርስቲያን “ከክርስትና ውጪ ያሉ እምነቶች የባጢል እምነቶች ናቸው” ብሎ ያምናል።

አንድ ሙስሊም “ከእስልምና ውጪ ያሉ እምነቶች ባጢል ናቸው።" ብሎ እያመነ, የክርስቲያኖችን በዓል አብሮ የሚያከብር ከሆነ፦

  ውሸታምና አስመሳይ ነው‼

አንድ ክርስቲያን “ከክርስትና ውጪ ያሉ እምነቶች ባጢል ናቸው።” ብሎ እያመነ, የሙስሊሞችን በዓል አብሮ የሚያከብር ከሆነ፦

  ውሸታምና አስመሳይ ነው‼

  የትኛውንም ኡስታዝ መስጂድ ውስጥ "ጀነት ሊገቡ የሚችሉት ሙስሊሞች ብቻ ናቸው። ከዝያ ውጪ ያሉት ከሳሪዎች ናቸው”፣

“አላህ በሚወደው ነገር እንጂ አላህ በማይወደው ነገር መተባበር ወንጀል ነው" ብሎ እያስተማረ፤

ሚዲያና አደባባይ ላይ ሲወጣ “መቻቻል ኢትዮጵያዊነት ነው” እያለ የክርስቲያኖችን በዓል የሚያከብር ከሆነ፦

ይህ ኡስታዝ ሳይሆን አጭበርባሪና ለሆዱ አዳሪ ነው‼

  የትኛውንም ቄስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ “ገነት የሚገቡት ክርስቲያኖች ብቻ ናቸው (ያመነ የተጠመቀ ይድናል, ሌላው ግን አይድንም)" ብሎ እያስተማረ፤

ሚዲያና አደባባይ ላይ ሲወጣ “መቻቻል ኢትዮጵያዊነት ነው” እያለ የሙስሊሞችን በዓል የሚያከብር ከሆነ

  እሱም አጭበርባሪና ሌባ ነው‼

አዎን‼

ሙስሊም ነኝ። ከእስልምና ውጪ ያሉ እምነቶች በአጠቃላይ ባጢል እንደሆኑ አምናለሁ። ከእስልምና ውጪ ያሉ የሰው ልጆች በአጠቃላይ እስልምናን ተቀብለው ከእሳት ድነው ጀነት እንዲገቡ እመኝላቸዋለሁ። በቻልኩትም እንዲሰልሙ እጥራለሁ።

ያሉበት እምነት ባጢል እንደሆነ ውስጤ እያወቀ ግን “እንኳን አደረሳችሁ” እያልኩ የውሸት ደስታ እየገለፅኩ እነርሱንም እራሴንም መዋሸት አልችልም‼‼

ክርስቲያን ነህ❓ "ከክርስትና ውጪ መዳኛ የለም" ብለህ ታምናለህ❓ ክርስትና አለ መቀበሌ ያሳስብሃል❓

እንግዲያውስ ና! ስለ ክርስትና አስረዳኝ፤ ስለ እስልምና ላስረዳህ‼

እንጂ፦

ክርስትና ባለ መቀበሌ እያዘንክ ከሆነና "ባጢል ላይ ነህ" የምትለኝ ከሆነ የእስልምና በዓላቶችን ሳከብር እንዴት "እንኳን አደረሰህ" እያልከኝ የውሸት ደስታ እየገለፅክ ራስህንም እኔንም እንዴት ትዋሻለህ❓❓❓

✍ልብ በሉ‼ አሁንም ልብ በሉ‼

ይህ ጉዳይ የፖለቲካ አስተሳሰብ አይደለም። የብሄር ውዝግብ አይደለም። የእምነት ጉዳይ ነው። የጀነትና የጀሀነም ጉዳይ ነው። እውነታውን አውርቶ እውነቱን ይዞ የሚኬድበት እንጂ በውሸት መቻቻልና መግባባት የሚኬድበት ነጥብ አይደለም‼

እሺ! እንዴት እንኗኗር❓❓

👇👇👇👇👇

በመጀመሪያ የጋራ ሀገር እንጂ የጋራ እምነት የለንም‼️ ሁላችንም ኢትዮጵያዊያኖች ነን።

«ኢትዮጵያዊ ወንድሞቼ» እንጂ

ሙስሊሞች «ክርስቲያን ወንድሞቼ»፣ ክርስቲያኖች «ሙስሊም ወንድሞቼ» የሚሉበት አግባብ አይኖርም።

እንደ ዜጋ በሀገር ልማት ላይ አብረን የምንሰራቸው ስራዎች ሊኖሩን ይችላሉ፤

እንደ እምነት ግን አብረን የምናከብረው እምነት የለንም።

ሁሉም የሰው ልጆች እስልምና የመቀበል ግዴታ አለባቸው; እስካልተቀበሉ ግን አንድነቱን ይወገዳል።

በማህበራዊ ኑሯችን እንገበያያለን፣ እንበዳደራለን፣ እንተባበራለን።

በእምነታዊ ጉዳይ ግን ከተቻለ ትክክለኛ በሆነው እስልምና አንድ መሆን; ካልተቻለ ግን አብሮ የሚከበር ምንም ዓይነት የእምነት በዓልም ይሁን ስርዓት አይኖርም።

ክርስቲያን ወላጆች፣ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች ካሉን በዝምድናችን ልክ እንዛመዳቸዋለን እንኗኗራቸዋለን።

በእምነታዊ ተግባራቸው ግን ምንም ዓይነት ተሳትፎ አይኖረንም።

👉ከታመሙ እንጠይቃቸዋለን።

👉ከቻልን እናግዛቸዋለን።

👉ካገኘን እናበላቸዋለን።

👉ከተራቆቱ እናለብሳቸዋለን።

👉ስጦታም እንሰጣቸዋለን።

👉ዝምድናቸውን እንቀጥላለን።

❌እንኳን አደረሳችሁ አንልም።

❌የማክበሪያ ቦታም አናፀዳም።

❌የበዓል ግብዣም አንቀበልም።

👆ስሜታችን ሳይሆን የጌታችን ትዕዛዝ ነው👇

📖{ وَوَصَّيْنَا ٱلْإِنسَٰنَ بِوَٰلِدَيْهِ حَمَلَتْهُ أُمُّهُۥ وَهْنًا عَلَىٰ وَهْنٍ وَفِصَٰلُهُۥ فِى عَامَيْنِ أَنِ ٱشْكُرْ لِى وَلِوَٰلِدَيْكَ إِلَىَّ ٱلْمَصِيرُ (14) وَإِن جَٰهَدَاكَ عَلَىٰٓ أَن تُشْرِكَ بِى مَا لَيْسَ لَكَ بِهِۦ عِلْمٌ فَلَا تُطِعْهُمَا وَصَاحِبْهُمَا فِى ٱلدُّنْيَا مَعْرُوفًا وَٱتَّبِعْ سَبِيلَ مَنْ أَنَابَ إِلَىَّ ثُمَّ إِلَىَّ مَرْجِعُكُمْ فَأُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ(15)}

"ሰውንም በወላጆቹ (በጎ እንዲያደርግ) በጥብቅ አዘዝነው፡፡ እናቱ ከድካም በላይ በሆነ ድካም አረገዘችው፡፡ ጡት መጣያውም በሁለት ዓመት ውስጥ ነው፡፡ ለእኔም ለወላጆችህም አመስግን በማለት (አዘዝነው)፡፡ መመለሻው ወደኔ ነው፡፡(14) ለአንተ በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህም አትታዘዛቸው፡፡ በቅርቢቱም ዓለም፤ በመልካም ሥራ ተወዳጃቸው፡፡ ወደእኔም የተመለሰን ሰው መንገድ ተከተል፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደ እኔ ነው፡፡ ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፤ (አልነው)፡፡(15)

   [አል_ሉቅማን:14–15]

  በዚህ አንቀፅም ይሁን በሌሎች አንቀፆች ላይ ከእስልምና ውጪ ካሉ ወዳጅ ዘመዶችም ይሁን ከአጠቃላይ ሰዎች ጋ በምን ዓይነት መልኩ መኗኗር እንዳለብን አላህ ያስተምረናል።

👉ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል ወደ እስልምና እንጣራቸዋለን።

👉የስጋ ዝምድና ወይም ጉርብትና የሚያገናኘን ከሆነ ለእነርሱ መጠበቅ ያለብን መብታቸው እንጠብቅላቸዋለን።

👉በቻልነው ያህል ማህበራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ድጋፍና እገዛ እናደርግላቸዋለን።

👉እስልምናችንን በሚጋጭ ጉዳይ ላይ ግን በምንም ነገር ቢያዙን አንታዘዛቸውም።

👉እምነታቸውን በሚመለከት ጉዳይ ላይ ምንም ዓይነት እገዛም ይሁን ትብብር አናደርግላቸውም።

👉ቢታመሙ እንጠይቃቸዋለን፣ ቢራቡ እናበላቸዋለን፣ ቢራቆቱ እናለብሳቸዋለን፤

ቢሞቱ ግን አጥበን ከፍነን አንቀብራቸውም‼

✍️እኛ ሙስሊሞች «በኢትዮጵያ ባህልና ወግ» መሰረት ሳይሆን

«በቁርኣን እና በሐዲስ» ህግጋት መሰረት ነው ህይወታችን የምንመራው‼

    🖊ሐምዱ ቋንጤ

          ከፉርቃን ሰማይ ስር

https://t.me/hamdquante

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group