8 month Translate
Translation is not possible.

ኢራን “እስራኤልን መቅጣት” ያለችው ዘመቻ ማብቃቱን ገለጸች።

እስራኤል ከሁለት ሳምንት በፊት በሶሪያ መዲና ደማስቆ በሚገኝ የኢራን ኢምባሲ ላይ ባደረሰችው የአየር ላይ ጥቃት ሁለት ወታደራዊ አዛዦችን ጨምሮ ዘጠኝ ኢራናዊያን መገደላቸው ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ በኢምባሲዋ ላይ ለደረሰው ጥቃት እስራኤልን እንደምትበቀል ስትዝት የቆየችው ኢራን መጠነ ሰፊ የድሮን እና ሚሳዔል ጥቃት ወደ ቴልአቪቭ መተኮሷን አስታውቃለች።

የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጥቃቱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ወደ እስራኤል ድንበር በርካታ ሚሳዔሎችን እና ድሮኖችን መተኮሱን አስታውቋል።

የኢራን አብዮታዊ ዘብ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ሞሀመድ ባግሪ እንዳሉት መግለጫ እስራኤል ለመቅጣት በሚል የተካሄደው ዘመቻ ማብቃቱን አስታውቋል፡፡

ይሁንና እስራኤል የአጸፋ እርምጃ ለመውሰድ ከሞከረች ግን ከእስካሁኑ የከፋ እርምጃ እንደሚጠብቃትም አስታውቋል፡፡

አሜሪካ ከዚህ ጥቃት ራሷን እንድታርቅ ያስጠነቀቁት ዋና አዛዡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ በቀጣይ እርምጃዎች ላይ አሜሪካ ጣልቃ ከገባች ግን በመካከለኛው ምስራቅ ያሉ የአሜሪካ ወታደራዊ ማዘዣዎች ጥቃቱ ኢላማ ይሆናሉ ሲልም አስጠንቅቀዋል፡፡

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በበኩላቸው ከኢራን የተሰነዘረባትን ከ300 በላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትታ መጣሏን አስታውቃለች፡፡

ሰው አልባ አውሮፓላኖቹ ጥቂት ጉዳት ብቻ አድርሰዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገራቸውን አየር ሀይል እና አጋር ሀገራትን አድንቀዋል፡፡

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሀገራቸው ከእስራኤል ጎን መሆኗን ገልጸው የቡድን ሰባት ሀገራት እንዲመክሩበት እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል፡፡

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group