Translation is not possible.

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ነውረኛ ተግባር

("ሼር" አድርጉት)

~

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከዒድ ጋር በሚጋጭ መልኩ የፈተና ፕሮግራም አውጥቷል። ዩኒቨርሲቲው በቅድሚያ ካሌንደር አይቶ ፕሮግራሙን ማዘጋጀት ነበረበት። ነገር ግን ዩኒቨርሲቲው ያወጣው ፕሮግራም ከዒድ ጋር በመግጠሙ እንደሚቸገሩ ሙስሊም ተማሪዎች ቢያሳውቁትም አሻፈረኝ እንዳለ ነው። ይሄ ውሳኔው ምናልባትም ጥፋቱ ሆን ተብሎ የተፈፀመ እንደሆነ እንድናስብ የሚያደርግ ነው። ምናልባት ጥፋቱ በአንድ ወይም በተወሰኑ አካላት የተፈፀመ ከሆነ የሚመለከተው ክፍል እንዲያስተካክል እንጠይቃለን።

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ደረጃቸውን የሚመጥን ቁመና ሊኖራቸው ይገባል። በኛ ሃገር ተጨባጭ ግን ዩኒቨርሲቲዎች ማለት በአመዛኙ ለሌሎች ክፍሎች ጥላቻ ያረገዙ አካላት ጭቆና የሚያራምዱባቸው የግፍ አፀዶች ናቸው። በተለይ ደግሞ የነዚህ ተቋማት ቀዳሚ ሰለባዎች ሙስሊሞች ናቸው። ይሄ መቋጫ ያጣና የረባ መሻሻል የሌለው ልማድ ለሌላው የህብረተሰብ ክፍል ምሳሌ መሆን የነበረባቸው ምሁሮች ተራማጅ ያልሆኑ ፍፁም ኋላቀሮች እንደሆኑ እንዲሁም የሃገር ተስፋ መሆን የነበረባቸው ተቋማትም የበሰበሰ መዋቅር የታቀፉ እንደሆኑ ያሳያል።

ለማንኛውም ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ እንዲህ አይነቱን ለሌሎች እሴት ንቀትን የሚያንፀባርቅ ኋላ ቀር አካሄድን ሊያርም ይገባል። በዚህ ጉዳይ ላይ የሚመለከታችሁ ሁሉ ሃላፊነታችሁን እንድትወጡ እናስታውሳለን። የዩኒቨርሲቲው ተግባር አንድምታው ከፕሮግራም ማዛባት ያለፈ ነው።

ሁላችሁም "ሼር" አድርጉት ባረከላሁ ፊኩም።

Bahir Dar University, Ethiopia

Ministry of Education Ethiopia

=

የቴሌግራም ቻናል

t.me/IbnuMunewor

Send as a message
Share on my page
Share in the group