✨أسلام عليكم ورحمة الله وبركاته
🌺ምስጋና ለአለማቱ ጌታ የተገባ ነው። እንደሚታወቀው የሁዘይፋ ኢብኑል የማን የሴቶች ጀመዐ በውስጡ ባቀፋቸው ዘርፎች አማካኝነት የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል ከነዚህ ዘርፎች መሀከል ዚያራ ሴክተር ግንባር ቀደሙ ነው።
ይህ ሴክተር በተለያዩ ቦታ የሚገኙ፤የሰው ፊትን ፈርተው ቤት ውስጥ ለተሸሸጉ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ድጋፍን ያደርጋል።50 ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለ 50 ሰው ግን ጌጡ ነው እና ከተባበርን ኢንሻአላህ ለብዙዎች እንደርሳለን።
ዕለተ ቅዳሜ የካቲት 24, 2024 በተደረገው ዚያራ ላይ የተሳተፋቹ የሁዘይፋ ኢብኑል የማን የሴቶች ጀመዐ አባላት በአጠቃላይ ከልብ እናመሰግናለን።
የዛሬው ባለታሪካችን እህት ፈቲያ ስትሆን የ4 ልጆች እናት ናት።አባታቸው ጥሏቸው በመሄዱ ልጆቿንም ለብቻዋ በማሳደግ ላይ ትገኛለች፤ በዚህ ጊዜ ኑሮ በከበደበት ሰዐት ያለ ደጋፊ ኑሮን መምራት በመክበዱ ሶስቱ ልጆቿ ትምህርታቸውን አቋርጠዋል፤ይህም የሆነበት ምክንያት ደግሞ የእናታቸው በተደጋጋሚ መታመም ነው።ሁለተኛ ልጇ የ14 አመት ታዳጊ እና የ 6ተኛ ክፍል ተማሪ ነበር።ነገርግን በእናቱ ተደጋጋሚ ህመም ምክንያት እና አሁን ያሉበት ቤት ለመውደቅ የተቃረበ በመሆኑ ከትምህርት ገበታው ርቆ ስራ በመፈለግ ላይ ነው፤
ከእናታቸው መታመም ሰበቡ ላያቸው ላይ ሊውድቅ የደረሰው በሸራ ከታጠረው መኖሪያ ቤታቸው የሚገባው ብርድና ውርጭ ነው።የሌሊቱን ብርድ ችለው በጋውን እንደምንም ተቋቁመው ያልፉታል፤ክረምቱ ግን በጣም ከባድ እና አሳሳቢ ነው።የሚጠለሉበት ሸራ ቤት ለመውደቅ ከመቅረቡም ጋር ጎርፍ ያስገባል፣ከእናት ህመም ጋር ተጨምሮ የክረምት መምጣት የልጆች አንድ ሀሳብ ሆኗል።ህመሟን የምታስታምምበት፣ልጆቿን ሰብስባ እረፍት የምታደርግበትን ለሷም ለልጆቿም ሰላም የሚሆናትን ማረፊያ ታገኝ ዘንድ ሁላችንም የበኩላችንን እንወጣ።
በዚህ ምንዳዎች በእጥፍ በሚባዙበት ወር እኛም ከምንዳው ተቋዳሽ እንሆን ዘንድ፤ልጆቿም ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሱ ዘንድ፣ለእናታቸውም እረፍት ይሰማት ዘንድ በምንችለው እንረባረብ፣
እህት ፈቲያን
✅በገንዘብ
✅በእህል
✅በአልባሳት
መደገፍ ለምትፈልጉ +251930594583 በመደወል የጀመዐውን በይተል ማል ማናገር ትችላላቹህ።
➡️ለበለጠ መረጃ በቴሌግራም @Niemtullah ላይ ጥያቄያችሁን ማቅረብ ትችላላቹህ፤
➡️በአካል መጥታቹም፣ያሉበት ሁኔታን አይታቹ ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉም በራችን ክፍት ነው።
ስለምታደርጉትም ድጋፍ በአላህ ስም እናመሰግናለን።
✅قال رسول الله ﷺ اتقوا النار ولو بشق تمرة.
በተምር ክፋይም ቢሆን እሳትን ተጠንቀቁ ። (ረሱል ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም)