Translation is not possible.

🌹መጣ እረመዷን🌹

ረመዳን መጣ ራህመት ተሸክሞ

ማን ይሁን ተቀባይ ፀባዩን አርሞ

🎋

አልሀምዱሪላሂ መጣልን ረመዳን

ከእሳት ጀሀነም ብንሞትም ለመዳን

🥀

ከወራቶች በላጭ አራተኛዉ አርካን

ግድ መሆኑንም ተገልፆዋል በቁርአን

🌾

ምድሩን አፍክታ ሰማዩን አድምቃ

ብቅ አለች ብቅ አለች ብቅ አለች ጨረቃ

🌴

ተራዊህ ተህጁዱ የሌሊት ሹክሹክታ

ሬድዋዉን ሽቶ የለይሉ ቆይታ

💐

አዝካር ሰለዋቱ የዱአዉ ትዉስታ

የወንድምን ናፍቆት ሙሀባዉ ትዝታ

🌸

አጀብ አንተ ትብስ ወጋችን ማሰሪያ

የመተዛዘኛ የአብሮነት መኖሪያ

🌼

ተቅዋን ሊያላብሰን የተኛን ሊያነቃ

የዝነቱ ወር መጣ ብቅ አለች ጨረቃ

🥀

በኢባዳ ወስዶ ደግሞ በአዝካሩ

በቁርአኑ ሸንጎ ተርቲብ እየቀሩ

🌷

ኸይሩ ሚን አልፊ ወር ማግኘት እየጎጉ

ለሊቱ በስቲግፋር በዱአ እያነጉ

🪻

የረመዳን ፀጋ በረካዉን ሽተዉ

ሲያነጉ ይፈጃል የከርመዉን ናፍቆው

🌲

የፆመኞች እንስጥ የአፍጥር ነገር

በብርጭቆ ዉሀ ሶስት ፍሬ ቴምር

ለንያ ነይተን ለማግኘት አጅር

🎄

አምና ከኛጋራ ስንት ሰዉ ነበረ አብሮን ያፈጠረ

ቀጠሮ ደርሶበት እንደ ወጣ ቀረ ቀብር ተሳፈረ

🌿

እረመዷን

የአንድነት የህብረት ቀለም

የከፍታ የፍካት አለም

አዲስ ንጋት የሩህ መስከረም

አገናኘን በፍቅር ዳግም

ሰበሰበን በፍቅር ዳግም

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group