Translation is not possible.

ለረመዿን ነፍስያችንን እናዘጋጅ‼

======================

ከፊት ለፊታችን ያንዣበበው ታላቁና የተከበረው የረመዿን ወር ሊገባ  ቀናት ብቻ ይቀሩታል።

በጣም ያስገረመኝና ያሳዘነኝ ነገር፤ እስከ ዛሬ ረመዿን ሊገባ ሲል ገና ከወር በፊት ቀደም ተብሎ ከረመዿን ጋር ተያያዥነት ያላቸው በርካታ መልዕክቶች በማኅበራዊ ሚዲያ ሲንሸራሸሩ ይስተዋል ነበር። የረመዿንን መድረስ ድባብም ያሟሙቁት ነበር። ዘንድሮ ግን ብዙም እያየሁ አይደለም። ጥሩ ይጽፉ የነበሩ ከፊሎች የሉም፣ ያሉትም ብዙዎቹ በሌላ ነገር ተጠምደዋል።

ለማንኛውም ከረፈደም ቢሆን ረመዿንን በዕውቀት ስንጾመው የተሻለ ነውና በአላህ ፈቃድ ቀሪ ጊዚያችንን ከርሱ ጋር ተያያዥነት ባላቸው ሃሳቦች ብናሳልፍ እንጠቀማለን። የተለያዩ ዳዕዋዎችን በማዳመጥ፣ ተያያዥነት ያላቸውን ጽሑፎች በማንበብና ያላወቅነውን ፈታዋ በመጠየቅ ረመዿንን እንጠቀምበት። ኢንሻ አላህ ከዛሬ ጀምሮ ከረመዿን ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሃሳቦች የተገራልልን ያክል አብረን እናነሳለን። ሌሎቻችሁም እንደዛ ብታደርጉና ምናልባትም በአንዳችን ሰበብ አንድ ሰው ያላወቀውን አሳውቀን ረመዿንን ባወቀው ቢሠራበት ከሚያገኘው ምንዳ ተካፋይ እንሆናለን።

በርካታ መልዕክቶችን በቋሚነት የምለቀው በቴሌግራም ቻነሌ ስለሆነ ይህን የቴሌግራም ቻነሌን መቀላቀል ትችላላችሁ።

👇👇👇👇

https://t.me/+M7JTzc1bH7k4OTVk

Telegram: Join Group Chat

Telegram: Join Group Chat

?ይህ የወንድማችሁ Zeyne Seid ቻናል ነው። በዚህ ቻናል ውስጥ ብዙ አይነት ትምህርቶችን ለማድረስ እሞክራላሁ ። ኢንሻአላህ ስህተቴን በቁርአን በሀዲስ ላረመኝ አላህ ይዘንለት እቀበላለሁ አድርሱኝ ? አላህ ዱንያዬም አኼራዬንም እንዲያሳምርልኝ ዱአ አድርጉልኝ ። ????? https://t.me/+M7JTzc1bH7k4OTVk
Send as a message
Share on my page
Share in the group