Translation is not possible.

❤️.........🐪 የግመሏ ፍቅር 🐪........

ስሟ " ቀስዋእ " ትባላለች ስያሜዋን ያገኘችው የጆሮዋ ጫፍ በጥቂቱ የተቆረጠ በመሆኑ ምክንያት ነው። ውልደቷ የ በኒ ቁሸይሽ ጎሳ መንደር ነው።  በጥቁርና በነጭ መልኮች መካከል (ወደ ነጭ ያደላች)  ግመል ናት።  

    በጥንካሬዋ፥በፍጥነቷ፥በቅልጥፍናዋና በትጋቷ ወደር ያልተገኘላት፤ በሠይዲና አቡበከር ለረሱል ﷺ የቀረበች ስጦታ  ታዛዥ ግመል ናት። አንድም ግመል በፍጥነት ቀድሞት አያውቅም . . . .

   ከዕለታት በአንዱ ቀን  የአንድ አዕራቢይ ግመል  የረሱሉል አሚንን ግመል ቀድማ ከፊት ፈረጠጠች። ግርምት ተፈጠረ፤አንድም ግመል ቀድሟት አያውቅም። በቅልጥፍና የሚግደራደራት አካል በመፈጠሩ ሁሉም አፈጠጠ። ነብዩምﷺ እንዲህ አሉ:-

«አላህ ይህንን ደንግጓል ፤ በዱንያ ላይ አንድም ነገር ከፍ አይልም በአንፃሩ ጊዜውን ጠብቆ ዝቅ የሚል ቢሆን እንጂ !!»

     ይህቺው የረሱል ግመል ከህልፈታቸው በኋላ ፍፁም ጤናዋ ራቃት ፤ ማንንም በጀርባዋ ለመሸከም፥ ማንንም ለማጓጓዝ ፍቃደኛ አልሆን አለች። በሀዘን ኩርምት፥ ጭምት አለች።  ከሞቱ በኋላ እህል ውሀ መቅመስ አልቻለችም። ለአንድ ወር ያህል አፏን ከምግብና ከእህል ከልክላ ሠነበተች። እጅግ ከማልቀሷ ብዛት ሁለት አይኖቿ ታወሩ

መገን ፍቅር!!

   ወዳጄ እያነገርኩህ ያለሁት ስለ ሚስቶቻቸው አልያም ስለ ባልደረቦቻቸው አይደለም፤ ቀስዋእ ስለተባለችው የነብዩ ﷺ ግመል ነው

ይህም ብቻ አይደለም  በሀዘን ፥በለቅሶ ፥በረሀብ፥ በጥማት ብዛት ተቆሳቁላ

"ያለ ረሱል  ﷺ ህይወት ለምኔ!" በማለት በ 14 ዓመቷ በናፍቆት እንደተንገበገበች ይህቺን ጠፊ አለም ተሠናበተች!!

ረሱል ﷺ ግመሏ ላይ ቁጭ ብለው ጀነትን አስከፍተው ይገባሉ ይህቺው ግመል ቀስዋእ ናት.

Send as a message
Share on my page
Share in the group