Çeviri imkansız.

👉 ክፍል አንድ

→ ፖርኖግራፊ(የወሲብ ፊልምና የብልግና ምስሎች)

     🔥🔥🔥  🔥🔥🔥  🔥🔥🔥  🔥🔥🔥

ማንም ይሁን ማን፣ እነዚያ በሙእሚኖች መካከል ጸያፍ ነገሮች እንዲስፋፉ የሚወዱና የሚያስፋፉ ወገኖች በቁርኣን ከባድ ዛቻ ተሰንዝሮባቸዋል፡፡

አላህ (ሱብሃነ ወተዓላ)እንዲህ ይላል በሱረቱል(አን ኑር አንቀፅ 19)

إِنَّ ٱلَّذِينَ يُحِبُّونَ أَن تَشِيعَ ٱلْفَٰحِشَةُ فِى ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ فِى ٱلدُّنْيَا وَٱلْءَاخِرَةِ وَٱللَّهُ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ

እነዚያ በእነዚያ ባመኑት ሰዎች ውስጥ መጥፎ ወሬ እንድትስፋፋ የሚወዱ ለእነሱ በቅርቢቱም በመጨረሻይቱም ዓለም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡ አላህም ያውቃል እናንተ ግን አታውቁም፡፡

ምንም እንኳን ቁርኣን ጸያፍ ነገሮችን በሙእሚኖች መካከል የሚያስፋፉ ሰዎችን አብዝቶ ቢያስፈራራቸውም ነገር ግን በተለያዩ መንገዶች በርካታ ጸያፍ ድርጊቶች ወደ ማህበረሰባችን ገብተዋል፡፡ ከነዚህም መካከል አንዱና አይደፈሬው የወሲብ ፊልም ነው፡፡ ይህም የብልግናዎች ሁሉ ጥግ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ያም ሆኖ ግን በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነትን አግኝቶ ሱስ እስከመሆን ደርሷል፡፡ የወሲብ ሲዲዎችም በከፍተኛ ብር እንደሚሸጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ሲዲ ሻጮችም በወሲብ ሲዲ ብዙ ሚባል ብር ያተርፉበታል፡፡ በርካቶቹ የወሲብ ፊልም ሱሰኞችም ከርሱ መጥፎ ልምዶች በማካበት ወደ ወሲባዊ እብደቶች ገብተዋል፡፡ «የወሲብ ንግድ ስሙ የካፊሮች ቢሆንም ብልግናውን በማየት ግን የጋራችን ሆኗል፡፡ ከቡና ቤት ሴቶች በላይ መጻፍ ያለበት የብልግና ታሪክ ያለው ግን የቤት ልጆች ላይ ነው፡፡ በዚህ ዓይነቱ ከገደብ ያለፈ ብልግና ውስጥ እንድንገባ ካደረጉን ነገሮች ውስጥ አንዱና ዋናው ምክንያት የነጮቹን የወሲብ ፊልም መውደዳችን ነው። መውደድ ብቻ አይደለም፤ ፈልገን ማየታችን እንጂ፡፡

ከቀደምት ኢማሞቻችን ሲወርድ ሲዋረድ እንደመጣሁ በየጁምዓው ኢማሙ ኹጥባውን ቀጥሎ ባለው ቁርኣናዊ አንቀጽ ሲቋጭ እንሰማለን፡-

   Surah An-Nahl,verses: 90

إِنَّ ٱللَّهَ يَأْمُرُ بِٱلْعَدْلِ وَٱلْإِحْسَٰنِ وَإِيتَآئِ ذِى ٱلْقُرْبَىٰ وَيَنْهَىٰ عَنِ ٱلْفَحْشَآءِ وَٱلْمُنكَرِ وَٱلْبَغْىِ يَعِظُكُمْ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ

አላህ በማስተካከል፣ በማሳመርም፣ ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፡፡ ከአስከፊም(ከማመንዘር)፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ፣ ከመበደልም ይከለክላል፡፡ ትገነዘቡ ዘንድ ይገስጻችኋል፡፡

ዑለሞቻችን እንደሚሉት የወሲብ ፊልምና መሰል ድርጊቶች በሙሉ አላህ(ﷻ)ከላይ ባለው አንቀጽ ውስጥ የከለከላቸው ሦስቱንም ነገሮች በውስጣቸው ይይዛሉ፡-ፋሒሻ(ጸያፍ)፣ ሙንከር(የተጠላ) እና በጊ(ድንበር አላፊነት)

  👉 ይ ቀ ጥ ላ ል...

         

ኢንሻ አላህ በቀጣይ የወሲብ ፊልምን የሚመለከቱ መረጃዎች እና እውነታዎች እለቀላችኋለሁ።

ሁላችንም በምችለው ሼር እናድርገው ቢያንስ ለ10 ጓደኞቻችን ሼር እናድርገው።

ይሄን በሽታ ብዙዎቻችን በድብቅ ስለሆነ ምንሰራው ሰዎችን ለማማከር እንፈራለን ስለዚህ ይሄ ጥሩ አጋጣሚ ስለሆነ በምንችለው ሼር እናድርግላቸው።

    👉👉👉ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር👈👈👈

      

  🔥በዝሙት አንዘምን የቴሌግራም ቻናል🔥

ይቀላቀሉን እንመካከር በመመካከር

      ህይወት ቀለል ትላለች

     👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/latekrebu_zina

منقول

Mesaj olarak gönder
Sayfamda paylaş
Grupta paylaş