Translation is not possible.

🌿ካንሰር ግን ምንድን ነው?

~ምንም ይህ በሽታ ከግዜ ወዲህ በስፋት ቢታወቅም ለረጅም አመታት 'ነቀርሳ' በሚል ስሙ በብዛት ይጠራ ነበር።

➡️ካንሰር ማለት በሰውነታችን ውስጥ ያሉ ጥቃቅን ህዋሶች (በጤና ግዜም ሰውነታችን የተገነባው ከነሱ ነው) እብደት ነው ብንለው ይቀላል።

~በተለያዩ እስካሁን በሚታወቁም ሆነ በማይታወቁ ምክንያቶች በሰውነታችን ክፍል ባለች አንዲት ህዋስ ወይም የህዋስ ቡድን ውስጥ የዘረመል ቀውስ ይፈጠራል ይህ ደሞ ያቺ ህዋስ ከመጠን በላይ እንድትባዛ ያረጋታል ይህ መባዛትም ወደ አይን የመታየት ደረጃ ላይ ይደርስና እብጠት ይፈጥራል።

~እነዚ በአይን የሚታይ እብጠት የፈጠሩት በሚሊዮን ብሎም በቢሊዮን የሚቆጠሩ ህዋሶች እንደ እብድ ውሻ ቦታቸውን ለቀው በቅርብም በሩቅም ወዳለ ሰውነታችን ክፍል ይጓዛሉ ማለት ነው። ይህም በሚሆንበት ግዜ ታማሚው እጅግ ይጎዳል። ለምሳሌ እነዚ ህዋሶች ከሳንባ ከተነሱ የሳንባ ካንሰር እንላቸዋለን፣ ከጡት ከተነሱ የጡት ካንሰር እንላቸዋለን።

~እነዚህን የካንሰር ህዋሶችም ለማጥፋት ቀዶ ህክምና፣ የመድሃኒት ህክምና (Chemotherapy) እና የጨረር ህክምና (Radiotherapy) እንጠቀማለን። ሆኖም ግን እንደየካንሰር ሁኔታው፣ አይነት እና የስርጭት መጠን የማገገም ብሎም የመዳን እድል ሊኖራቸው ቢችልም አብዛኞቹ ግን ታካሚውን ለከፋ የጤና እክል ብሎም ሞት ይዳርጋሉ።

      ዶ/ር መላኩ አባይ ፤ የስነ ደዌ ህክምና ስፔሻሊስት

Send as a message
Share on my page
Share in the group