Translation is not possible.

ወስን

~

በጫትና በመጠጥ ሱስ ቤትህን እያፈረስክ፣ ልጆችህን እየበተንክ፣ የራስህንም ሆነ የቤተሰብህን ጥሪት እያወደምክ ያለኸው ወገኔ ሆይ! አይበቃም ወይ? እስከ መቼ ቁልቁል እያምዘገዘገህ ባለ ደባል ሱስ ተሸንፈህ ትኖራለህ? ሰው እንዴት የሰው እጅ ጠባቂ ሆኖ ይቅማል? ሰው እንዴት ይህንን የአህያ ሽንት የመሰለ እር.ኩስ መጠጥ ይጠጣል? ሰው እንዴት በገዛ ፈቃዱ ቀጥ ብሎ ወጥቶ እየተንገዳገደ ይመለሳል? ግዴለህም አላህን ፍራ! ለጤናህ አስብ። ለቤተሰብህ አስብ። ለትዳርህ አስብ። ለልጆችህ አስብ። በየሰው ቤት እየተንከራተቱ ገንዘብ ለሚልኩልህ አስብ። ስንት መከራ፣ ስንት ፈተና፣ በረሃ፣ እሳት፣ የሰው ፊት፣ ... አይተው፣ አሳር በልተው የሚልኩትን ገንዘብ ለማይረባ ቅጠል ስታውለው አያሳዝኑህም? ከምንም በላይ ደግሞ ለኣኺራህ አስብ። ወላሂ ከቆረጥክ ማቆም ይቻላል። ብቻ አንተ ወስን። ከዚያም ሰበብ አድርስ። ከልብ ካለቀሱ እምባ አይገድም።

Send as a message
Share on my page
Share in the group