ترجمہ ممکن نہیں

⚫️👉*የጁመዓ መልእክት*

📩

*ነቢዩ ሙሀመድ ﷺ *የሚከተለውን ብለዋል፦*

_ፀሀይ ከወጣችበት በላጩ ቀን የጁሙአ ቀን ነው በዛች ቀን ነቢዩላህ አደም_ _ተፈጠረ፣ጀነትንም ገባ፣ከጀነትም ወጣ፣ የቂያማ ቀንም በጁሙአ ቀን እንጂ አትቆምም_

   *📚<ሙስሊም _ ዘግቦታል*

_በጊዜ ወደ መስጅድ መሄድ ነቢዩ ﷺ የሚከተለውን ብለዋል፦_

_የጁማዕ ቀን ላይ በእያንዳንዱ መስጅዶች በር ላይ መጀመሪያ የመጣውን መጀመሪያ ላይ ቀጣይ የመጣውን በተርታ የሚመዘግቡ መላኢካዎች አሉ ልክ ኢማሙ ሚንበር ላይ በተቀመጠ ጊዜ መዝገባቸውን ዘግተው ኹጥባ ለማዳመጥ ይመጣሉ። መጀመሪያ ሰአት ላይ የመጣ ሰው ምሳሌው ልክ ግመል ሰደቃ እንዳወጣ ነው፤ከዛ ከብት እንደሰደቀ ነው፤ከዛ ሙክት በግ እንደሰደቀ ነው፣ከዛ ዶሮ እንደሰደቀ ነው፣ ከዛ እንቁላል እንደሰደቀ ነው።_

*📚[ቡኻሪ ዘግቦታል]*

                                                  *አላህ የጁማአ ቀን  አስመልክቶ እንዲህ ይላል*

  فَإِذَا قُضِيَتِ الصَّلَاةُ فَانتَشِرُوا فِي الْأَرْضِ وَابْتَغُوا مِن فَضْلِ اللَّهِ وَاذْكُرُوا اللَّهَ كَثِيرًا لَّعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

_ሶለቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ፡፡ ከአላህም ችሮታ ፈልጉ፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፡፡ ልትድኑ ይከጀላልና፡፡_

وَإِذَا رَأَوْا تِجَارَةً أَوْ لَهْوًا انفَضُّوا إِلَيْهَا وَتَرَكُوكَ قَائِمًا ۚ قُلْ مَا عِندَ اللَّهِ خَيْرٌ مِّنَ اللَّهْوِ وَمِنَ التِّجَارَةِ ۚ وَاللَّهُ خَيْرُ الرَّازِقِينَ

*ንግድን ወይም ዛዛታን ባዩ ጊዜም ቆመህ የተዉህ ሲኾኑ ወደእርሷ ይበተናሉ፡፡ አላህ ዘንድ ያለው ዋጋ ከዛዛታም ከንግድም በላጭ ነው፡፡* «አላህም ከሰጪዎቹ ሁሉ ይበልጥ ሲሳይን ሰጭ ነው» በላቸው፡፡

_📚{ጁማዓህ-10-11}_

የጁማዕ ሶላት ሁለት ረካዐዎች ያሉት ፈርድ ሶላት ነው።

*አንድ ሰው" ዘግይቶ ቢመጣና ሁለተኛውን ረከዐ ከጀማዓጋር ከሰገደ ቀሪውን አንድ ረከዐ አሟልቶ መስገድ አለበት ። አንድ ሰው" በጣም ዘግይቶ በመድረሱ የጁማዓው ሶላት ሙሉ በሙሉ ያመለጠው እንደሆነ አራት ረከዐዎች ፈርድ የዙሁር ሶላት መስገድ ይኖርበታል። የጁማዓ ሶላት የዙሁር ሶላት ምትክ ናት።*

                                            *_ሶላት አለን-ነብይ የማውረድ ትሩፋት_*

قال صلى الله عليه وسلم « مَنْ صَلَّى عَلَيَّ صَلاَةً صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشْرًا »

_ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዳሉት‘መን ሶላ ዓለየ ሶላተን ሶለልሏሁ ዐለይሂ ቢሃ ዐሸራ’ ‹‹በኔ ላይ አንድ ጊዜ ሶላዋት ያወረደ አላህ በርሱ ላይ አስር ጊዜ ሶለዋት ያወርድለታል_

وقال صلى الله عليه وسلم : « لاَ تَجْعَلُوْا قَبْرِي عِيْدًا وَصَلُّوْا عَلَيَّ؛ فَإِنَّ صَلاَتَكَ تَبْلُغُنِي حَيْثُ كُنْتُمْ »

*ሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዳሉት:* _መቃብሬን የባዕል ማዕከል አታድርጉት ፡፡በኔ ላይም ሶለዋት አውርዱ፡፡ የትም ሆናቸሁ ሶለዋት ብታወርዱ ይደርሰኛል፡፡_

وقال صلى الله عليه وسلم : « الْبَخِيْلُ مَنْ ذُكِرْتُ عِنْدَهُ فَلَمْ يُصَلِّ عَلَيَّ »

*እንዲህ ሲሉም ተናግረዋል፡*_ስስታም ማለት ከርሱ ዘንድ እኔ እየተወሳሁ በኔ ላይ ሶለዋት ያላወረደ ነው፡፡_

وقال صلى الله عليه وسلم : « إِنَّ لِلَّهِ مَلاَئِكَةً سَيَّاحِيْنَ فِي اْلأَرْضِ يُبَلِّغُوْنِي مِنْ أُمَّتِي السَّلاَمَ »

*እንዲህ ሲሉም ተናግረዋል:* _ለአላህ ተጓዥ መላኢኮች አሉት፡፡ ምድር ላይ ከኡመቴ የሚላክልኝን ሰላምታ ለኔ ያደርሳሉ፡፡_

وقال صلى الله عليه وسلم : « مَا مِنْ أَحَدٍ يُسَلِّمُ عَلَيَّ إِلاَّ رَدَّ اللهُ عَلَيَّ رُوْحِيَ حَتَّى أَرُدَّ عَلَيْهِ السَّلاَمَ »

_ነብዩ(ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡: “አንድ ሰው ሰላምታ ሲልክልኝ አላህ ነፍስ ይዝራብኝና ምላሽ_ እሰጠዋለሁ፡፡

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group