12 month Translate
Translation is not possible.

*★መልካችን ከአላህ ነው*

*صورنا وملامحنا من الله*

—————————

አዎ የቆዳችን ከለር፣ የተክለ ሰውነታችን ቅርጽ ፣ የቁመታችን መጠን እንዲሁም የፊታችን ገጽታ የእኛ ምርጫ ሳይሆን የጥበበኛው አላህ ድንቅ ሥራ ነው ።

አላህ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ይላል: —

((እርሱ ያ በማሕጸኖች ውስጥ እንደሚሻ አድርጎ የሚቀርጻችሁ ነው፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡))

{هُوَ الَّذِي يُصَوِّرُكُمْ فِي الْأَرْحَامِ كَيْفَ يَشَاءُ ۚ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ}(ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 6)

መልክ ፣ የቆዳ ከለር፣ ቁመት የአላህን አዋቂነትና ጥበበኛነትን የሚገልፁ ስለሆኑ የሱን ስራ አስተንትኖ እሱን ከማመስገንና ከማደነቅ ውጭ የአላህ ስራ የተገለፀበትን አካል አያኮራምም አያሳፍርምም ።

★ስለዚህ ሰው ወዶና ፈቅዶ ባላመጣው የአካል ገጽታው አይመሰገንምም አይወቀስምም ።

★ ሰዎችን ከፍ ወይም ዝቅ ለማድረግ መልካቸውን ወይም ቁመናቸውን መመዘኛ ማድረግ እጅግ የኋለ ቀርነትና መሀይምነት ምልክት ነው ።

★ አላህ ሰውን በሰውነቱ አክብሮ የሚገባውን ሀቁን ከሚጠብቁ መልካም ባርያዎቹ ያድርገን 🤲🏻 አሚን ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group