Translation is not possible.

ቁጥር አንድ 1/4

⭕️ ክፍል አንድ👇

  የተደበቀው የሸይጧን ወጥመድ

(የሃራም ፍቅር/ ቦይ-ገርል ፍሬንድ)

 بــســم الــلــه الــرحــمــن الــرحــيمــ

             الحمد الله رب العالمين

ውድ እህቴ የሃራም ፍቅር ግኑኝነትን በጣም በሩቁ ልትጠነቀቂው ይገባል ምክንያቱም በዚህ ሰዓት ብዙ እህቶችሽ እየተፈተኑበት የሚገኙው ከባድና አስቸጋሪ ፊትና ነው አሁን ባለንበት ዘመን የተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ተበራክተዋል ለምሳሌ ዋሳፕ ፌስቡክ ኢሞ ቴሌግራም እና መሰል የሚዲያ አፖች አሉ በነዚህ ቴክኖሎጂዎች ከሚመጡ ፊትና እራስሽን ማራቅ ይኖርብሻል። ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ብዙ እህቶች በነዚህ ሶሻል ሚዲያዎችና በመፃፃፍ ስልክ በማውራትና በተለያዩ መንገዶች ከተለያዩ ወጣቶች ጋር የሃራም ፍቅር ግኑኝነት ፈጥረዋል። ለምን እህቶች ተብለው ሲጠየቁ ምን ችግር አለው ለቀልድ ለመዝናናት እና ጊዜ ለማሳለፍ ብቻ ነው ብለው ይመልሳሉ።  ውድ እህቴ ይሄንንስ የሃራም የቀልድ ግኑኝነት እንድትቀርቢው ማን ነው የፈቀደልሽ? ውድ እህቴ ይሄ መንገድ ሃራም ነው። አላህን ፍሪ! እንዲህ አይነቱ የሃራም ፍቅር ግኑኝነት በኢስላም በጥብቅ የተከለከለ ነው እስከዛሬም ወደፊትም በሸሪዓው አልተፈቀደም።

 

ወድ እህቴ ከየትኛውም አይነት ወጣት ጋር የሶሻል ሚዲያ የሃራም ፍቅር ግኑኝነት ልትርቂ ይገባል ፍቅር አይደለም ብለሽ ልታወሪም አይገባም በፁሁፍ የምታወሪው በስልክም ምታወሪውን ካለ ልታቆሚ ይገባል። ትዳር ፈልገሽም ከሆነ በዚህ በሃራም ምንገድ መሆን የለበትም ብዙዎች ትግስት እያጡ ወደ ሃራም ፍቅር ይገባሉ ግን መፍትሄው ይሄ አይደልም ማወቅ ያለብሽ ነገር በሃራም ፍቅር የጀመርሽው ግኑኝነት መጨረሻ ላይ ልታገቢው ብትችይ እንኳ ለትዳርሽ ጥፍጥናን አታገኝም ምክንያቱም በሁለት ጥንዶች መሃል መዋደድንና መተዛዘንን የሚያደርገው አንድ አላህ ብቻ ነው። አላህም ደግሞ ቃል የገባልን በሃላል ትዳር ለሚይዙት ብቻ ነው።  ውድ እህቴ አላህን አስከፍትሽ በሃራም ባመጣሽው ትዳር እንዴት ደስተኛ ህይወት ልትኖሪ ትችያለሽ?። ይሄ በጭራሽ አይሆንም ካገባሽው በኋላ ባጭር ግዜ ውስጥ በትናንሽ ነገር ትዳራችሁን ይበጠበጣል እና ቆም ብለሽ አርቀንሽ በማሰብ ከዚህ የሃራም ግኑኝነት ልትርቂ ይገባል ለጊዚያዊ ስሜት ብለንሽ ዱንሽንም አኼራችንም አታበላሸው። አላህን አምፆ መቸም የተረጋጋ ህይወት የለም

  🎁 ውድ እህቴ በዚህ የሃራም ፍቅር ውስጥ የተደበቀውን እውነታ እነግርሻለሁ

  በትኩረት ተከተይኝ

 

🔥 የመጀመሪያው እውነታ፦ ምን አልባት አንችን ሊወድሽ ይችላል ግን ካንችም ውጭ ሌሎችን ብዙ ሴቶችንም ይወዳል ያወራል ይህ ማለት አንችም ላይ ይጫወታል ካንችም ውጭ ብዙ ሴቶች ጋር ግኑኝነትን ይፈጥራል። ሲጀመር አንችን በሃራም መንገድ እያወራ ለአላህ ሳይታመነ እንዴት ላንቺ ሊታመን ይችላል።? ይሄ የመጀመሪያው የተረጋገጠ እውነታ ነው። በሃራም መንገድ ምንም አይነት ዋስተና የለንም።

 

🔥 ሁለተኛው እውነታ ደግሞ ምንም ጋብቻ ሚባለውን ነገር አያስበውም አላማውም ግቡም የለውም ይህ ማለት ወደ ጋብቻ አይገፋፋሽም። ምን አልባት ስለ ትዳር ሊያወራሽ ይችላል ግን የሚነግርሽ በዚህ ሰአት ማግባት እንደማይችል ነው ይሄ ደግሞ አንቺን ለሃራም እስኪያመቻችሽ ሁኔታዎችን እየጠበቀ መሆኑን አትርሺ።!

   → ሦስተኛው እውነታ 📌 ይ ቀ ጥ ላ ል

💥 አልሃምዱሊላህ ይህ ፁሁፍ ለብዙዎች የመመለስና ወደ ሃራም እንዳይገቡ ጥንቃቄ የማድረግ ሰበብ ሆኗል። በውስጥ መስመር ለምናውቃቸው ሁሉ ሼር የማድረግ ሃላፊነት አለብን። ምን አልባት የአንድ ሰው የመመለስ ወይም ጥንቃቄ የማድረግ ሰበብ ልትሆን እንችላለን። አላህ የፈለገውን ይመራበታል።

  

ወንድማችሁ  ሙሂድን ሰኢድ

https://t.me/menhaj_Asselefiy101A

Telegram: Contact @menhaj_Asselefiy101A

Telegram: Contact @menhaj_Asselefiy101A

✍️✍️✍️ ?ሁሉንም ያማከለ ቢፈህሚ ሰለፍ ሙሀዶሯ :አጫጭር ሀድሶች ግጥሞች :እንድሁም ቁርአን ቲላዋ የሚለቀቅበት ቻናል ነዉ joine Share በማድረግ የአጂሩ ተካፋይ ይሁኑ
Send as a message
Share on my page
Share in the group