Translation is not possible.

ኪታባቸውን ተንተርሰው ወደቁ

❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️

በሳኡዲ የሸህ ኡሰይሚን ደረሳ የነበሩ፤ሱደይስን ተጅሪድ ያቀሩ ታላቁ ዓሊም ሀገር ውስጥ ከገቡ በኋላ በርካቶችን እያስተማሩ ነበር። አሁን አስኮ በድር መስጅድ ኸጢብ ከመሆናቸው በፊት አፍንጮ በር የሚገኘው አቅሷ መስጅድ ያቀሩ እንደነበር የሚታወቁት በነሲሀ ቲቪም ሲያስተምሩ ይታወቃሉ።

ትናንት ምሽት ኪታባቸውን ተንተርሰው ለልጃቸው የገዙትን ዳቦ በትነው የወደቁበት ቦታ ላይ የዳቦው ፌስታል በደም ጨቅይቶ አየነው። ከጀርባቸው ሲመቱ አይነ በሲሩን አረቡን ቤቱ እየሸኙት ነበር።

ወደ አረቡ ቤት አቅንተን የሆነው ሁሉ ሲቃ እየተናነቀው አጫወተን። አረቡ እንደነገረን ከመግሪብ እስከ ኢሻ ተፍሲር ሲያቀሩ አመሹ። ለዚያውም ሱረቱል ዙመርን ሲያብራሩ አመሹ።

ሁሌም እንደሚያደርጉት መስጅድ በር ላይ ሲዋክ የሚሸጠውን አይነ በሲሩን አረቡን ለመሸት ጠበቁት። አረቡ ሁሌ እንደሚያደርገው «ኡስታዝ አይጠብቁኝ ይሂዱ» ይላቸዋል። እሳቸው እሽ አይሉም። ከኢሻ በኋላ ለአረቡ ምርኩዝ ናቸው። እንጀራ አይበላም ለሚሉት ለልጃቸው ዳቦ ገዝተው አረቡን ቤቱ እየመሩ አስገብተው ነው ወደቤታቸው የሚገቡት።

ትናንትም አይነ በሲሩን አረቡን እየመሩ ወደቤታቸው ሲሄዱ መታጠፊያ አሳቻ ቦታ ላይ ከቅርብ ርቀት በተተኮሰ ሽጉጥ ከጀርባቸው በኩል ተመተው የወደቁ ሲሆን በወቅቱ አረቡም ራሱን ስቶ አብሮ ወድቆ ነበር። በተመቱበት ሰዓት በአካባቢው መብራት ጠፍቶ እንደነበርና ከወደቁ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ መብራት መምጣቱን የአካባቢው ሰዎች ነግረውናል።

እዳ ያስጭንቃቸው እንደነበር እና በሽማግሌዎችም የተሰጣቸው ጊዜ አጭር በመሆኑ ያሳስባቸው እንደነበር የተወሰነውን ተበድረው ከፍለው ቀሪውን ለመክፈል ቤታቸውን ለመሸጥ እንዳሰቡ ነገር ግን የበድር መስጅድ ጀመዓዎች ቤቱ ከመሸጡ በፊት ትላንት ፈጅር ላይ ለመስጅድ ጀመአ ዛሬ እሁድ ገቢ ለማሰባሰብ እቅድ ተይዞ እንደነበር ነገሩን።

እናንተ የአላህ ባሮች ኢማማችንን ሸኻችንን ከየቲም ልጆቻቸው ጋር እና ከእዳቸው ጋር ለኛ ትተው ተገድለዋል።

ከቀብራቸው በፊት እዳ ለመክፈል እየተንቀሳቀሱ ያሉ ኮሚቴዎች አካውንት የከፈቱና የገለጹ ስለሆነ ፖሊስ ገዳዩን አጣርቶ ለህዝብ ይፋ እስኪያደርግ የመስጅድ ኢማም እንደመሆናቸው መጠን መጅሊስ በቅርብ ርቀት ዜናው ከተሰማበት አንስቶ ከሚመለከተው አካል ጋር ሲከታተል እንደነበረው ሁሉ ማህበረሰቡም ደግሞ እዳውን እንዲከፍል ጥሪ ቀርቧል።

የኢማማችን ባለቤት በቅርብ ጊዜ ወደ አኸራ የተሻገሩ በመሆኑ የቤቱ አስተዳዳሪ አባት ሸይኽ አላህ ይዘንላቸው ያለውን ክፍተት እንሙላ።

አስተባባሪ ኮሚቴ ስም የተከፈለ የሂሳብ አካውንት

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

የአካውንት ስም:- ጀሚል ሁሴን ፣ ሲሩ ሀሰን እና አብዱ ዑስማን

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:- 1000592716309

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group