Translation is not possible.
❌ ከሃዲያኖች ለበዓላቸው ያዘጋጁትን ምግብ መመገብ አይቻልም‼️
 
ጥያቄ ፦
 
ሙስሊሞች የሁዳዎች ፣ ነሳራዎችና ሙሽሪኮች ለበዓላቸው በሚል ያዘጋጁትን ምግብ መመገብ ወይም ለበዓላቸው ምክንያት ያዘጋጁትን ስጦታ መቀበል ይቻልላቸዋልን ?
 
መልስ ፦
 
❌ ሙስሊም ለሆነ ሰው የሁዳዎች ፣ ነሳራዎችና ሙሽሪኮች ለበዓላቸው በሚል ያዘጋጁትን ምግብ መመገብ አይቻልለተም‼️
 
❌ በተጨማሪ ሙስሊም ለሆነ ሰው የሁዳዎች ፣ ነሳራዎችና ሙሽሪኮች ለበዓላቸው በሚል ያዘጋጁትን
ስጦታ ከነሱ መቀበል አይቻልለተም‼️
 
ምክንያቱም ፦ ይህን ነገር በማድረግ ውስጥ እነሱን ማክበር ይገኝበታል። እንዲሁም የዕምነታቸውን ምልክት ግልፅ በማድረግና ቢድዓቸውን በማሰራጨት ላይ ከነሱ ጋር ትብብር ማድረግም ይሆናል። እንዲሁም በበዓላቸው የተነሳ የሚያገኙትን ደስታ መጋራትም አለበት።
 
🔥🔥🔥 በእርግጥም ይህን ነገር ማድረግ በዓላቸውን "ዒድ" አድርጎ ወደ መያዝ የሚጎትት ነው !!!!!
 
👉👉👉 ... ወይም ደግሞ አምልኮትን ወደ መቀየር አነሰ ቢባል ምግባቸውን ወደ መንካትና በበዓላቸውና በበዓላችን ስጦታን ወደ መለዋወጥ (ይወስዳል !!!)
 
🔥🔥🔥 ይህ ደግሞ ፈተናና በዲናችን ላይ አዲስ ነገር መፍጠር ነው‼️
 
በእርግጥም ከነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ተረጋግጦ እንደመጣው ፦
 
✅ « በዚህ ጉዳያችን (ዕምነታችን) ላይ ከሱ (ከእስልምና) ያልሆነን አዲስ ነገር የፈጠረ የሆነ ሰው ስራው ተመላሽ ይደረግበታል !!!!! »
 
❌ ለበዓላቸው በሚል ምክንያት ለነሱ ስጦታን ማበርከት እንዳልተቻለው ሁላ ( ለበዓላቸው በሚል ያዘጋጁትንም ምግብ መመገብ አይቻልም‼️)
 
(ለጅነቱ አዳሂማ (22/398))
 
📝 … ኢስማኤል ወርቁ
 
https://t.me/amr_nahy1
Telegram: Contact @amr_nahy1

Telegram: Contact @amr_nahy1

ይህ ቻናል በመልካም ማዘዝንና ከመጥፎ መከልከልን ዓላማው በማድረግ ቁርኣንና ሐዲስን በሰለፎች ግንዛቤ በመመርኮዝ የተለያዩ አስተማሪና ገሳጭ ምክሮች የሚተላለፍበት ነው። አስተያየት ለመስጠት= @esmael9
Send as a message
Share on my page
Share in the group