Translation is not possible.

ጦርነቱ ከተጀመረ ጀምሮ እስራኤል ዛሬ ከፍተኛውን ወታደራዊ ኪሳራ አስተናግዳለች !

በአንድት እሁድ 14 ወታደሮቹ የተገደሉባት ሀገር ከፍተኛ ውጥረቷ እየጨመረ በቤኒያሚን ኔታኒያሁ ላይ የሚደርሰው ጫናም እየበረታ ይገኛል !

ዛሬ ኔታኒያሁ ማቅ ለብሶ በደረሰው የወታደሮቹ ውድመት መግለጫ ለመስጠት ተገዷል።

" እጅግ ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰብን ይገኛል ግና እስከምናሸንፍ ድረስ የግድ መዋጋት አለብን " ሲልም ኔታኒያሁ እብሪቱን ዳግም ደግሞታል ።

ይህ በእንድህ እንዳለ ከፍተኛ ምትን ያስተናገደው የእስራኤል ጦር ቤይት ሀኑንን ጨምሮ ከሶስት የጋዛ ቦታዎች አፈግፍጓል ።

የእስራኤል ጦር በአሁኑ ሰአት ወደ ፊት ከመግፋት ይልቅ ማፈግፈግ ላይ ይገኛል ። የሙጃሂዶቹ ምትም ተጠናክሮ ቀጥሏል ።

በጣም የሚያሳዝነው ግን የእስራኤል ጦር በምድር በተሸነፈ ቁጥር እስራኤል ሽንፈቷን የምታካክሰው ንፁንን በአየር በመጨፍጨፍ መሆኑ ነው ። በአንድ ቀን ውስጥ በርካታ ኪሳራን ያስመዘገበቺው እስራኤል እርሱን ለማካካስ በፈፀመቻቼው እረፍት የለሽ የአየር ድብደባዎች በ 24 ሰአት ውስጥ ከ 160 በላይ ንፁሀን ተገድለዋል ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group