Translation is not possible.

በርግጥ ይሄን ቃዒዳ ልናውቀው ይገባል!!

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይምያህ እንዲህ ይላሉ፦

أهل البدع يعتقدون ثم يستدلون وأهل السنة يستدلون ثم يعتقدون

«የቢድዓ ባለቤቶች ያምናሉ ከዛ ለዛ ለተሳሳተ (ጥመት) እምነታቸው መረጃ ይፈልጋሉ። የሱና ባለቤቶች መረጃ ይይዛሉ ከዛ እምነት አድርገው ይይዛሉ!!»

ይህ ታዲያ ሌላን አካሄድ እምነት አድርገው የሚሄዱና ያን ጥሩ ለማስመሰል የሚጥሩ እንጅ፤ አንድ ሠው ተመልሻለሁ ሲልና ንግግሩን ሲያስተካክል ሲጀመር በመረጃ በተናገርክ ለምን ተሳሳትክ ማለት አይደለም። ከቶውንም ስህተቱ የቃላት ስህተት ብቻ ሲሆን ጉዳዩ የተለየ ይሆናል።

ሸይኹል አልባኒ የሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይምያህን ንግግር ምን ማለት እንደሆነ ተጠይቀው «የቢድዓ ባለቤቶች መጀመሪያ ያምኑና ያን (የተሳሳተ እምነታቸውን) ጥሩ ለማስመል መረጃ በማፈላለግ የሚጥሩ ናቸው» ብለዋል።

🎤#ምንጭ፦ ከድምፃቸው የተወሰደ!!

የቴሌግራም ቻናል፦

https://t.me/Abdurhman_oumer/6270

.

Send as a message
Share on my page
Share in the group