በሪድዋን ቃል ኪዳን ወቅት የአላህ መልእክተኛ ﷺ ለአንድ ሙስሊም ደም ሲሉ ሰሃቦችን በሞት ላይ ቃል አስገቡ።
ረሱል ﷺ በ6ኛው ዓ.ሂ ዑምራን አስበው ወደ መካ ጉዞ ጀመሩ። መዲናን 340 ኪ.ሜ አካባቢ ርቀው ከተጓዙ በኋላ ግን ጉዳዩ ካሰቡት በተቃራኒ ሆነ። ከጅምሩ በቀጥታም በተዘዋዋሪም ለዐረብ ጎሳዎች ለዑምራ እንጅ ለጦርነት እንዳልተንቀሳቀሱ እንዲያውቁት አድርገው ነበር።
ይሁን እንጂ ቁረይሾች ሙስሊሞች ወደ መካ መቃረባቸውን ሲሰሙ ለማገድና ለመዋጋት መሰለፍ ጀመሩ። ረሱልምﷺ ዑስማንን (ረ.ዐ) ወደ ቁረይሽ በመልእክተኝነት ላኩት።
ዑስማንም አባን በተባለ ባለውለታ ሰው ከለላነት ወደ መካ በመግባት በታዘዘው መሰረት «የመጡት ለዑምራ አንጂ ለጦርነት እንዳልሆነ» ለአቡ ሱፍያንና በዙሪያው ላሉ ሹማምንት አሳወቀ።
ቁረይሾች ግን ጉዳዩን ክብራቸውን የሚያወርድ መስሎ ስለታያቸው ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ። ለዑስማንም «ጠዋፍ ማድረግ ከፈለግክ ማድረግ ትችላለህ» አሉት። እርሱም «ወላሂ ረሱል ያላደረጉትን ጠዋፍ እኔ አላደርገውም!» ብሎ ግብዣቸውን ውድቅ አደረገባቸው።በዚህ ጊዜ ዑስማን ታገተ።
ወደ ረሱልﷺ ዘንድም «ዑስማን ተገደለ» የሚል ዜና ደረሰ። የአላህ መልእክተኛም ﷺ ለአንድ ሙስሊም ደም ሊበቀሉ መሳሪያም ዝግጅትም ሳይኖር ሰሃቦችን ቃል አስገቡ።
የዚድ ኢብኑ አቢ ዑበይድ ሰለማህ ኢብኑል አክወዕን (ረዐ) ጠየቀው ፦ «የአላህ መልእክተኛን ﷺ የሑደይቢያህ (የሪድዋን) ቀን በምን ላይ ነበር ቃል የገባችሁላቸው? ሰለማም መለሰ ፦ «በሞት ላይ ነው ቃል የገባንላቸው! » (ቡኻሪይ ዘግበውታል)
በሞት ላይ ቃል የሚገባው ግዙፍ ጦርን ለመጋፈጥ ነው። ሳንሸሽ እየተዋጋን ለመሞት ብለው ሰሀቦች ቃል ገቡላቸው። ይህ ሁሉ የሆነው ለአንድ ሙስሊም ደም ለመበቀል ነበር።
የዶላር ኡለሞች ዛሬ ላይ ሙስሊም ሴትና ህፃናት በሺዎች ሲረግፉ አርፋችሁ ተመቀጡ ይላሉ። ሲቀጥልም ይህ ሁሉ ውድመት የመጣው በሙስሊሞች ጥፋትና « አቅምን አለማወቅ» እንደሆነ ለማሳመን ይውተረተራሉ።
መልእክተኛው ﷺ የመጡበት ዲን ግን በውርደት ከመኖር በክብር መሰዋትን የሚጣራ ዲን ነው! ለዚህም ነው ከመዲናቸው ርቀው በሰው ሀገር ላይ መሸሻ በሌለበት ቦታ በዒዝ ላይ ለመሞት ቃልኪዳን የተቀበሉት።
ይህንንም ድንቅ ጀብድ አላህ ወዶ ቁርኣን አወረደ ። ሲያልፍም በዚያ ቃል ኪዳን ላይ የተሳተፈ 1400 ሰሃባ ሁሉ እሳት ላይነካው ቃል ተገባለት!
«ከምእምናኖቹ በዛፊቱ ሥር ቃል ኪዳን በሚጋቡህ ጊዜ አላህ በእርግጥ ወደደ፡፡ በልቦቻቸውም ውስጥ ያለውን ዐወቀ፡፡ በእነርሱም ላይ እርጋታን አወረደ፡፡ ቅርብ የኾነንም መክፈት መነዳቸው፡፡ »
(አልፈትሕ 18)
የአላህ መልእክተኛ ﷺ አንዲህ አሉ፦ « ከዛፏ ስር ቃልኪዳን ከገባ አንዱም እሳት አይገባም» (ቲርሚዚይ፣አቡዳውድ፣አሕመድ)
ቁረይሾች ሙሐመድና ባልደረቦቹ በሞት ላይ ቃልኪዳን መጋባታቸውን ሲሰሙ ውሳኔያቸው ስላስፈራቸው የ«እንደራደር» መልእክተኛ ላኩ።በዚህም ምክንያት የሑደይቢያ ስምምነት የተባለው ታሪካዊ ስምምነት ተፈፀመ።የሁለቱ ብርሃኖች ባለቤት ዑሰማን ኢብኑ ዐፋንም በሰላም ተመለሰ።
ካሀዲያን ካንተ የሚፈሩት መሳሪያህን ሳይሆን ቁርጠኝነትህን ነው።እነርሱን ከመዋጋት ተስፋ እንደቆረጥክ ያወቁ ቀን ውርደት ያኔ ነው የሚጀምረው።
ሑደይቢያ ለመካ 50/60 ኪሜ ነው የሚርቀው። ደጀን የሚሆነው ህዝብ የሌለው 1400 ሰራዊትን ቁረይሾች በመካ ዙሪያ ካሉ አጋር ዘላን አረቦች ጋር ሆነው ሊጨርሱ የተመቸ ነበር። ነገር ግን ለዑምራ የመጣ ሰሃባ ለሞት ቃል እንደገባ ሲሰሙ ቁረይሾች ነገሩ እንደማያዋጣቸው መከሩ።
የተዋረድነው አንችላቸውም ያልን ቀን ነው ።ዑለማኡ ዲናሪ ወዶላር ሲሕር አድርገውብን እንጅ ኢስላም የእምቢተኝነት ዲን ነበር!
ቴሌግራም ፦ t.me/ismaiilnuru
Comment has been successfully reported
The post has been successfully added to your timeline!
You have reached your limit of 100000 friends!
File size error: The file exceeds the allowed limit (9 GB) and can not be uploaded.
Your video is being processed,
We’ll let you know when it's ready to view.
It's impossible to upload the file: This file type is not supported.
We have detected adult content on the uploaded image,
therefore we have declined the uploading process.
To get a verification (tick) on the Islamic social network Umma Life, you must meet at least one of the following criteria: 1. Social network activity: Participants seeking verification must be active users of the social network. At least one useful message must be posted per day, and the message topics can be non-religious. 2. A well-known Islamic blogger or Muslim: If you are a well-known Islamic blogger or Muslim, even if your activities are not related to religious topics on the Internet, you can also apply for verification. 3. A large number of subscribers or active religious pages: If you have a lot of subscribers on social networks or you actively manage useful religious pages, this can also be a basis for getting verified. If you meet at least one of these criteria, submit an application for verification on the Islamic social network Umma Life via private message https://ummalife.com/ummalife and your account will be reviewed by the social network administration.