Translation is not possible.

አስቸካይ የትውልድ አድን ጥሪ🚨

ባሳለፍነው ህዳር 5 ቀን 2016 ዓም ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአፍሪካ ከካሪቢያንና ከፓሲፊክ የተውጣጡ ሀገራት ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት የሚቆይ የንግድና ኢኮኖሚ ትብብር ስምምነትን ከአውሮፓ ህብረት ጋራ ሳሞዋ በምትባል ሀገር በፈረሙ ወቅት አገራችን ኢትዮጵያም ይህንኑ ስምምነት ተቀማጭነታቸው ብራሰልስ በሆኑ አምባሳደV አማካኝነት በፊርማዋ አጽድቃለች፡፡ ይህ አደገኛ ይዘቶች ያሏቸውን አንቀጾች የያዘው ስምምነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ ከሚቀጥለው ጥር ወር ጀምሮ ወደ ትግበራ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡

 

ይህ የትብብር ስምምነት በውሥጡ የያዛቸውን አስራ ሁለት ዋና ዋና አደገኛ ይዘቶችን ጠቅልለው የሚይዙ የተወሰኑ ሀሳቦች ለመጥቀስ ያህል ፡-

 

ሀ) የሀገር ሉዓላዊነትን የሚጥሱ አንቀጾች በግልጽ መቀመጣቸው፣

 

⭕️ለ) ግብረሰዶማዊነት፣ የጾታ መቀየርና፣¸ውርጃና ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርትን የመሳሰሉ እኩይ አጀንዳዎች በሰብዓዊ መብት ሽፋንና በሌሎች አሳሳች ሀረጎች ተሰውረው የገቡበት መሆኑ፣

 

ሐ) ግብረሰዶማዊነት በርካታ ቀውሶች ማለትም በአካል፣ በሥነልቦናና በማህበራዊ ህይወት ላይ የሚያስከትልና ለሀገር ደህንነትም አደጋ መሆኑ፣

 

መ) የወላጆችን መብት የሚጥስና የኢትዮጵያዊ ቤተሰብ እሴቶችን የሚንድ መሆኑ፣

 

ሠ) የሀገራችንን ሀይማኖት፣ባህልና እሴቶች የሚንዱ ጸያፍ ልምምዶችን እንድንቀበል በሰብዓዊ መብት ሽፋንና በእርዳታ ስም የምንገደድበትና ለዘመናዊ ባርነት ወይንም ቅኝ አገዛዝ ታልፈን የምንሰጥበት መሆኑ፣

 

በአጠቃላይ ይህ አዲስ የአጋርነት ስምምነት ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡና ትውልድንና ብሎም ሀገርን እጅግ የሚጎዱ በርካታ አንቀጾች የተካተቱበት መሆኑ ለሀገራችን ህዝብ ዕድገትን ሳይሆን ውድቀትንና ከፍተኛ የሞራል ዝቅጠትን የሚያስከትል መሆኑን በሚገባ ተረድተናል፡፡

 

በተጨማሪም ከተጠበቀው ውጭ ሀገራችን ይህንን ስምምነት በመፈረJ የተጋረጠብንን እጅግ አሳሳቢ አደጋ ለመቀልበስ አስፈላጊ የሆኑ ሰላማዊና ህጋዊ መንገዶችን ሁሉ በመጠቀም መንግስት ትኩረትን እንዲሰጠው ማድረግ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡

 

በመሆኑም ይህ የመንግስት ውሳኔ እንደገና ተጠንቶ ውሳኔው እንዲቀለበስ ማለትም ስምምነቱ አስፈላጊው ሁሉ ማስተካከያ እስኪደረግበት ድረስ ወይንም እጅግ አደገኛ የሆኑት አንቀጾች ተነቅሰው ወጥተው የማንቀበላቸው መሆናችንን በይፋ ማሳወቅ (Submission of an Interpretive Declaration) እስከምንችል ድረስ የምንወዳት ሐገራችን ኢትዮጵያ ፊርማዋን በመሰረዝ ከስምምነቱ ራሷን እንድታገልል በሐገራችን ከፍተኛው የሥልጣን አካል ለሆነው ለተከበረው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለሐገሪቱ መሪ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በታላቅ አክብሮት እጅግ አስቸኳይ ጥሪን እናደርጋለን፡፡

 

የዚህንም ስምምነት አደገኛ አንቀጾችንና በኤክስፐርቶች የተሰጠውን ትንታኔ የያዘ ዶኩመንት በአባሪነት ያቀረብን መሆናችንንም በታላቅ አክብሮት እንገልጻለን፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group