Translation is not possible.

አሰላሙአይኩም !

እናንተ ሰላም እንደዋላችሁ ተስፋ አደርጋለሁ ። ለመሆኑ ጋዛስ እንደት ዋለች ? በአጭር በአጭሩ

፨ ጦርነቱ ዛሬም ተፋፍሞ ሲቀጥል እስራኤል ተጨማሪ ሟች ወታደሮችን ይፋ አድርጋለች ። በዛሬው እለት ቢያንስ ከ 10 በላይ ወታደሮቿ የተገደሉባት እስራኤል በአየር ድብደባ የጋዛ ንፁሀንን ስትጨፈጭፍ ውላለች ።

፨ በጋዛ ምድር ከፍተኛ ኪሳራን እየተከናነበች የምትገኘው ወራሪዋ እስራኤል ከሀማስ ጋር ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ጥሪ አቅርባለች ። የእስራኤል ፕሬዚዳንት ኢሳቅ ሄርዞግ ዛሬ ባቀረበው ጥሪ በጋዛ ያሉ ታጋቾች እንዲለቀቁ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ለማድረግ ዝግጁ ነን ብሏል።

፨ ነገር ግን ሀማስ በበኩሉ በሰጠው መግለጫ የእስራኤልን ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ጥሪ እንደማይቀበል አሳውቋል ። ሀማስ ከእስራኤል ጋር ለመነጋገርና ተኩስ ለማቆም ቅድመ መስፈርት አድርጎ ያስቀመጠው እስራኤል በጋዛ ላይ የምታደርሰውን የአየር ድብደባ ስታቆም ብቻ ነው ብሏል ። ከዚያ ውጭ ግን የጋዛ ንፁሀንን እየጨፈጨፉ ስለ ታጋቾች መለቀቅ መነጋገር በፍፁም የማይሆን ነው ብሏል ።

፨ አሜሪካ የእስራኤልን መርከቦች ለመጠበቅ አለምአቀፍ የጦር ግንባር መስርታለች ። የየመን ሁታዎች የእስራኤልን መርከቦች መፈናፈኛ ማሳጣታቸውን ተከትሎ ነው አሜሪካ አለምአቀፍ ጦር ያቋቋመቺው ። ይህ አሜሪካ መራሽ ሀይልም ከአሜሪካ ፣ ከእንግሊዝ ፣ ከባህሬይን ፣ ከካናዳ ፣ ፈረንሳይ ፣ ጣሊያን ፣ ኔዘርላንድ ፣ ኖርዌይ ሲሸልስና ስፔይን የተውጣጣ ነው ። ከሁሉ የሚገርመው ግን መናፍቃኗ ሀገር ባህሬን የዚህ ፀረኢስላም ጦር አባል መሆኗ ነው ።

፨ የየመን ሁቲዎች ይህንን ጦር መመስረቱን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ ማንም ሀይል ከጋዛ ወንድሞቻችን ጎን ቆመን እንዳንዋጋ ሊያደርገን አይችልም ። በእስራኤል ላይ የምናደርሰውን ጥቃት የምናቆመው እስራኤል በፍልስጤማውያን ወንድሞቻችን ላይ የምታደርሰውን ጥቃት ስታቆም ብቻ ነው ብለዋል ። ለዚህም መሞት ለእኛ ደረጃችን ነው ሲሉም አክለዋል !

፨ ይህ በእንድህ እንዳለ ሀማስና ሂዝቡሏህ ዛሬ በእስራኤል ላይ የተቀናጀ የሚመስል ጥቃት ሲፈፅሙ ነው የዋሉት ። በዚህም ሂዝቡሏህ በእስራኤል ላይ በፈፀመው የሮኬት ጥቃት ታንኮችን ሲያወድም ወታደሮቿንም ገድሏል ። ሀማስ በበኩሉ ባደረሰው የሮኬት ጥቃት በርካታ ውድመትን ዛሬ ማድረሱ ተነግሯል ።

ቴሌግራም

👉 t.me/Seid

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group