Translation is not possible.

🔥👉ክፍል ሁለት

•አካላዊ ወይም ስነ ልቦናዊ ጉዳት ማድረስ፡-ጂኖች በሰዎች ላይ አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ

-ሀይለኛ ፍርሀት መልቀቅ፡፡

-ብዥታ እና ማስመሰል፡፡

-ስዎችን ማጣላት እና ማለያየት በተለይ ባል እና ሚስት፡፡

-ጭንቀት፡፡

-ማሳበድ፡፡

-የሚጥል በሽታ፡፡

-የሰውነት ክፍሎችን ሸባ ማድረግ ለምሳሌ እጅ እና እግር፡፡

-መካንነት እና ግዜውን ያልጠበቀ ደም መፍሰስ፡- ከወር አበባ እና ከወሊድ  ዉጭ ደም መፍሰስ፡፡

• በንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ፡-ቤት ማቃጠል፣ድንጋይ እና ሌሎች ነገሮችን ወደ ሰዎች ቤት በመወርወር ሰዎችን ማወክ ወዘተ…፡፡

• ጂኖች ለምን ሰዎችን ያጠቃሉ

• ጂኖች ሰዎችን በተለያዩ ምክንያቶች ሊያጠቁ ይችላሉ፡-

-ሰዎች በቢድዓ እና ሺርክ ሲዘፈቁ ፡- ሰዎች በሽርክ እና በቢድዓ ምክንያት በጂን ሊጠቁ ይችላሉ ለምሳሌ ከአላህ  ውጭ ለሆነ አካል ማረድ ለጂን፣ለቀብር እና ለመሳሰሉት፤ በተጨማሪም ለጂኖች ሲሰግዱ እና ዛር ቆሌ እያሉ የተለያዩ  ሽርክ እና ሀራም የሆኑ ነገሮችን ሲፈፅሙ ጂኖች በሰዎቹ ላይ አቅም ይኖራቸዋል በመጨረሻም ሊያጠቋቸው ይችላሉ፡፡

- ከሰው ጋር ፍቅር ስይዛቸው፡- ጂኖች ከሰው ጋር ፍቅር ልይዛቸው ይችላል ለምሳሌ ወንድ ጂን ከሰው ሴት  እና ሴት ጂን  ከሰው ወንድ ጋር ፍቅር ሊይዛቸው ይችላል፤ በዚህ ግዜ ካፈቀሩት ሰው አካል በመግባት ሰውየውን ሊያጠቁት ይችላሉ፡፡

-ያለ ምክንያት ሰዎችን ሊያጠቁ ይችላሉ፡፡

-በቀል፡-ሰዎች በጂኒዎች ጉዳት ሲያደርሱ  ጂኒዎች ሊበቀሉ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ  ቢስሚላህ ሳይል ሙቅ ዉሃ ማፍሰስ፣ጉድጓድ ላይ መሽናት፣ቢስሚላህ ሳይል ከፍታ ካለው ቦታ ላይ መዝለል እና በነዚህ ቦታዎች  ላይ ጂኒዎች ቢኖሩ በሰውየው ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡

-ሀራም ላይ መዘፈቅ፡-ለምሳሌ ሀራም የሆነ የፍቅር ግኑኝነት መመስረት፣ አጅነቢ ከሆኑ ተቃራኒ ፆታዎች ጋር አላስፈላጊ መግባባቶች እና ግኑኝነቶች፡፡

  • በጂን የተያዘ ሰው የሚያሳየው ምልክት

  • በንቃት ግዜ የሚያሳየው ምልክት፡-

-ቁርአን ሲቀሩ ወይም ሲሰሙ  መተኛት፣ የድብርት እና የህመም ስሜት የሚሰማን ከሆነ

ወይም  መጨነቅ  እና ቁርአንን  መጥላት፡፡

-ዒባዳ ስያደርጉ መሳነፍ እና የድብርት ስሜት የሚሰማን ከሆነ፡፡

-የባህሪ ለውጥ ማሳየት መነጫነጭ፣በጣም መቆጣት እና መናደድ፡፡

-ያለ ምክንያት መፍራት፣ማልቀስ፣መጨነቅ፡፡

-ሸባ መሆን(ሜዲካል ምክንያት ሳይኖር) እጅ፣ እግር ወይም ሌሎች የሰውነት ክፍል፡፡

-ለሴት ደም መፍሰስ ከወር አበባ ውጭ

-ቋሚ የሆነ የራስ ምታት(ሜዲካል ምክንያት ሳይኖር)

-መፀዳጃ ቤት ለረጂም ስኣታት ቁጭ ማለት

-ብቸኝነት መውደድ

-ያለ ምክንያት ሰውን መጥላት ወዘተ…

-በእንቅልፍ ግዜ የሚያሳየው ምልክት

-በተደጋጋሚ የሚያስፈራ ህልም ማየት እና መቀባዠር፡- የሚያሥፈሩ ነገሮችን ማየት ለምሳሌ እባብ፣ትላልቅ አስፈሪ ነገሮችን ማየት፣ከከፍተኛ ቦታ መውደቅ፣ በህልሙ/ሟ በተደጋጋሚ የሚያስፈራት/ው ሰው ማየት(ጂኖች ሰዎችን ስያፈቅሩ የሚከሰት ነው)ማለትም በህልም በተደጋጋሚ ግኑኝነት ማድረግ፡፡

  እነዚህ ምክንያቶች ያሉት ሰው ሁሉ በጂን ተይዟል ማለት አይደለም በሌሎች ምክንያቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡

      (አላህ የላቀና ይበልጥ አዋቂ ነው)

https://ummalife.com/Meryemhassen

Meryem hassen Hadra | UmmaLife

Meryem hassen Hadra | UmmaLife

Send as a message
Share on my page
Share in the group