Тарҷума мумкин нест.

🔸የሴቶች ፈተና

🔹 ኢብኑ ከሲር በ 278 አመተ ሂጅራ ላይ የተከሰተ ክስተትን ሲያነሱ እንዲህ ይላሉ ፦

አብደህ ቢን አብድ አረሂም የተባለው በዚህ አመት ነበር የሞተው ።

ኢብኑል ጀውዚ ሲያወሱ ይህ እደለ ቢስ ሮም ሀገር ላይ አብዝተው ጂሀድ ከሚያደርጉ ሙጃሂዶች አንዱ ነበር ። በሮም ሀገር ውስጥ በነበረ አንድ ጦርነት ላይ ሙስሊሞች ተከበው ሳለ በአንድ ምሽግ ላይ ከሮም ሴቶች መካከል አንዷን ይመለከትና ይፈተንባታል። ከዛም አንቺን ለማግኘት መንገዱ ምንድን ነው ?? ብሎ ሲጠይቃት " ክርስቲያን ልትሆንና ወደኔ ልትመጣ ነው " አለችው ። ለዚህም ጥያቄዋ እሺ ብሎ ምላሽ ሰጣት ። ሙስሊሞችም በዚህ በጣም ተጨነቁ ይህ ድርጊቱም በጣም ከበዳቸው !

እሱም በዚህ ሁኔታ ከዚች ሴት ጋር እያለ ከጊዜ በኃላ ሙስሊሞች በዛ ምሽግ ላይ ሲያልፉ ጠየቁት ፦

" አንተ እገሌ ቁርዓንህ ምን ሆነ ?? እውቀትህ ምን ሆነ ?? ፆምህስ ?? ጂሀድህስ ?? ሰላትህስ ምን ሆኑ !? "

እሱም እንዲህ አላቸው ፦ " ቁርዓንን እንዳለ ከዚች አንቀፅ ውጭ ያለውን እንደረሳሁት እወቁ

{رُّبَمَا يَوَدُّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَوْ كَانُوا۟ مُسْلِمِينَ ذَرْهُمْ يَأْكُلُوا۟ وَيَتَمَتَّعُوا۟ وَيُلْهِهِمُ ٱلْأَمَلُ ۖ فَسَوْفَ يَعْلَمُونَ}

«እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ ቀን) ሙስሊሞች በኾኑ ኖሩ በብዛት ይመኛሉ። ተዋቸው ይብሉ፤ ይጠቀሙም፡፡ ተስፋም ያዘናጋቸው፡፡ በእርግጥም መጥፎ ፍጻሜያቸውን ያውቃሉ»

ከእነሱም ( ከክርስቲያኖች) ንብረትም ልጅም ኑሮኛል"

በመጨረሻም በክርስትና አቋሙ ሞተ

📒 البداية والنهاية 『 11/69』

Send as a message
Share on my page
Share in the group