Translation is not possible.

ለአላህ ብላችሁ በትኩረት ሁሉንም ክፍሎች አንብቧቸው በጣም መሰረታዊ የሆነ ርዕስ ነው።

👉ክፍል አንድ  👉ጂን 

            بــســم الــلــه الــرحــمــن الــرحــيمــ

                         الحمد الله رب العالمين

ጂን;- ማለት ስውር ወይም ድብቅ ማለት ነው፡፡ ጂን የተባሉበት ምክንያት ለእኛ ስለ ማይታዩን እና ከኛ የተደበቁ ስለሆኑ ነው፡፡ በእነሱ ማመን ከኢልመል ገይብ የሚመደብ ሲሆን በእነሱ ማመን ግዳታ ነው፡፡ የእነሱን መኖር ማስተባበል ኩፍር(ክህደት)ነው፡፡ ጂኖች ልክ እንደ ሰዎች አማኞች፣ መልካም እና ጥሩ የአላህ ባርያዎች የሆኑ አሉ ፤ እንዲሁም ካሃዲዎች እና መጥፎዎችም አሉ፡፡ ጂኖች የተፈጠሩት ከእሳትነው፡፡

وَالْجَانَّ خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ مِن نَّارِ السَّمُومِ

‹‹ጃንንም(ከሰው) በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው፡፡›አል ሂጅር 27

• በቅድምያ እነዚህን ማጤን ይኖርብናል!!

    وَمَا هُم بِضَارِّينَ بِهِ مِنْ أَحَدٍ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ

  ‹‹እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልኾነ በርሱ አንድንም ጎጂዎች አይደሉም፡፡ ›› አል-በቀራህ 102

إِنَّ كَيْدَ الشَّيْطَانِ كَانَ ضَعِيفًا

  ‹‹የሰይጣን ተንኮል ደካማ ነውና፡፡››  አን-ኒሳእ 76

إِنَّمَا ذَٰلِكُمُ الشَّيْطَانُ يُخَوِّفُ أَوْلِيَاءَهُ فَلَا تَخَافُوهُمْ وَخَافُونِ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

‹‹እንዲህ የሚላችሁ ሰይጣን ብቻ ነው፡፡ ወዳጆቹን ያስፈራራችኋል፡፡ አትፍሩዋቸውም፡፡ ምእምናንም እንደኾናችሁ ፍሩኝ፡፡ ›› አል-ኢምራን 175

وَإِن يَمْسَسْكَ اللَّهُ بِضُرٍّ فَلَا كَاشِفَ لَهُ إِلَّا هُوَ ۖ وَإِن يَمْسَسْكَ بِخَيْرٍ فَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

  ‹‹አላህም በጉዳት ቢነካህ ለእርሱ (ለጉዳቱ) ከእርሱ በቀር ሌላ አስወጋጅ የለም፡፡ በበጎም ነገር ቢነካህ እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ ›› አል አንዓም 17

إِنَّ عِبَادِي لَيْسَ لَكَ عَلَيْهِمْ سُلْطَانٌ ۚ وَكَفَىٰ بِرَبِّكَ وَكِيلًا

  «ባሮቼ በእነሱ ላይ ፈጽሞ ላንተ ስልጣን የለህም፡፡ መጠጊያም በጌታህ በቃ፡፡»አል ኢስራእ 65

إِنَّ عِبَادِي لَيْسَ لَكَ عَلَيْهِمْ سُلْطَانٌ إِلَّا مَنِ اتَّبَعَكَ مِنَ الْغَاوِينَ

  «እነሆ ባሮቼ በእነሱ ላይ ላንተ ስልጣን የለህም፡፡ ከጠማሞቹ የተከተለህ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡»አል ሂጅር 42

አላህ(ﷻ)በቁርአን እንደነገረን ሰይጣን በመልካም ባሮች ላይ ምንም ስልጣን አና አቅም እንደለለው እና በአላህ ፍቃድ እንጂ መጉዳት እንደማይችሉ ማመን እና መገንዘብ ይኖርብናል፡፡

•ጂኖዎች የሚያደርሱት ጉዳት ጂኖች በሰዎች ላይ የተለያዩ ጉዳቶች ማድረስ ይችላሉ ይህ ስንል ግን በአላህ ፍቃድ እንጂ ምንም አይነት ጉዳት ሊያደርሱ አይችሉም፡፡

•ከትክክለኛው መንገድ ማጥመም ፡- የሰው ልጆችን ትክክለኛውን መንገድ(ኢስላምን)እንዳይዙ፣አላህን በብቸኝነት እንዳያመልኩ በተለያዩ አቅጣጫ በመምጣት ያሳስታሉ ይህም ዋነኛ ስራቸው ነው፡፡ ሸይጧን እንዲህ ሲል ነበር የፎከረው

قَالَ رَبِّ بِمَا أَغْوَيْتَنِي لَأُزَيِّنَنَّ لَهُمْ فِي الْأَرْضِ وَلَأُغْوِيَنَّهُمْ أَجْمَعِينَ إِلَّا عِبَادَكَ مِنْهُمُ الْمُخْلَصِينَ

‹‹ኢብሊስ)አለ «ጌታዬ ሆይ! እኔን በማጥመምህ ይኹንብኝ ለነርሱ በምድር ላይ(ኀጢአትን) እሸልምላቸዋለሁ፡፡ ሁሉንም አጠማቸዋለሁም፡፡ ከነርሱ ፍጹሞቹ ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ፡፡» አል-ሂጂር 39-40

قَالَ فَبِمَا أَغْوَيْتَنِي لَأَقْعُدَنَّ لَهُمْ صِرَاطَكَ الْمُسْتَقِيمَ ثُمَّ لَآتِيَنَّهُم مِّن بَيْنِ أَيْدِيهِمْ وَمِنْ خَلْفِهِمْ وَعَنْ أَيْمَانِهِمْ وَعَن شَمَائِلِهِمْ ۖ وَلَا تَجِدُ أَكْثَرَهُمْ شَاكِرِينَ

‹‹ስለአጠመምከኝም ለእነርሱ በቀጥተኛው መንገድ ላይ በእርግጥ እቀመጥባቸዋለሁ» አለ፡፡ «ከዚያም ከስተፊቶቻቸው ከኋላቸውም ከቀኞቻቸውም ከግራዎቻቸውም በእርግጥ እመጣባቸዋለሁ፡፡ አብዛኞቻቸውንም አመስጋኞች ኾነው አታገኛቸውም»(አለ)፡፡ ››አል-አዕራፍ 15-17

       (አላህ የላቀና ይበልጥ አዋቂ ነው)

አካላዊ ወይም ስነ ልቦናዊ ጉዳት ማድረስ

   👉በክፍል ሁለት ይጠብቁን

        👉 ይቀጥላል👈

https://ummalife.com/Meryemhassen

Meryem hassen Hadra | UmmaLife

Meryem hassen Hadra | UmmaLife

Send as a message
Share on my page
Share in the group