Наган дахаан йохтахам.

ትክክለኛው ስኬት‼

==============

✍ አንድ ሰው ስኬታማ ነው የሚባለው ዘመናዊ መኖሪያ ቤትና ዘመናዊ መኪና ስላለው ወይም ባለስልጣን ወይም ዝነኛ… ስለሆነ አይደለም። በጥቅሉ ስኬታማነት በቁሳዊ መለኪያዎች አይለካም።

ትክክለኛው ስኬታማነት ምን እንደሆነ አላህ በተከበረው ቃሉ በቁርኣን ላይ እንዲህ ሲል ነግሮናል፦

(كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوْنَ أُجُورَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۖ فَمَن زُحْزِحَ عَنِ النَّارِ وَأُدْخِلَ الْجَنَّةَ فَقَدْ فَازَ ۗ وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا مَتَاعُ الْغُرُورِ)

«ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በትንሣኤ ቀን ብቻ ነው፡፡ #ከእሳትም_የተራቀና_ጀነትን_የተገባ_ሰው_በእርግጥ_ምኞቱን_አገኘ፡፡ ቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ መሳሪያ እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡»

[ኣሊ ዒምራን: 185]

በእርግጥም ከጀሀነም እርቆ ጀነት መግባትን ከመታደል በላይ ምንኛ ያማረ የምኞት መሳካት አለ!

እንደ ሙስሊም ultimate ጎላችን ይህ ነው። ለዱንያ የቱንም ያክል ብንለፋ ሄደን ሄደን ለአኺራችን ሰበብ ከሆነን ነው ትርፋማነቱ።

አላህ ከጀሀነም የሚያርቀንንና ለጀነት መግባት ሰበብ የሚሆነንን ንግግርና ተግባር ያግራልን።

foll𝕠𝕨 𝕞𝕪 𝕡𝕒𝕘𝕖 👇

Send as a message
Share on my page
Share in the group