Табасаранан алхьа кха дац.

አላህየ አንተ በልቅናህ ይሁንብህ የመናዊያንን አልቃቸው !!!

ለካስ ወንድማማችየትን ላወቀው ወንድምነት እንደዚህ ከባድ ነው ! የመናዊያን ደግሞ የወንድምነት ውሀልክ ሆነው ሳያቸው ልቤን ማረኩኝ ! ቀናሁባቸው አሳዘኑኝም !!!

ደካማነትና ድህነት ሳይበግራቸው ፤ የቦታ እርቀት ሳይከልላቸው ስለፍልስጤማዊያን ወንድሞቻቼው የሚሆኑትን ሳይ ውስጤ ይነካል !

የፍልስጤም ወንድሞቻችንን የምትገድል ሀገር ከቶ በቀይ ባህር እንደት ታልፋለች ብለው የወራሪዋን ሀገር መርከብ ማሳደድ ከጀመሩ የቆዩት የመናዊያን ወንድሞቼ አሁን የትግል ኢላማቸውን ከፍ አድርገው " የየትኛውም ሀገር መርከብ ይሁን ወደ እስራኤል እስከሄደ ድረስ አንለቀውም " ብለው ቃል በገቡት መሰረት ወደ እስራኤል የሚጓዙ መርከቦችን እያሳደዱ እያጠቁ ይገኛሉ ። ለምን ሲባል - ለወንድማማችነት !!!

በላኢላሀኢለሏህ ገመድ ላይ ላለች ወንድማማችነት !!!

ይህንን ሲያደርጉ ከነአሜሪካ ጋር ከነ እስራኤል ጋር ከአውሮፓውያን ጋር እንደሚላተሙ ጠፍቷቸው ነው እንዴ ? በጭራሽ !!!

ግን ለወንድማማቾነት ሲሉ የሚከፍሉት መስዋዕትነት እንጅ !!!!

የፍልስጤም ወንድሞቻቼው ሞት አሳዝኗቸው ፤ የመስጅዶቻቼው ውድመት አንገብግቧቸው ፤ የወንድሞቻቼው ስቃይ እረፍት ነስቷቸው እንጅ !!!!

የመናዊያን በእስራኤል መርከቦችን ወደ እስራኤል በሚሄዱ መርከቦች ላይ እያደረሱ ባለው ጥቃት መርከቦቹ የአትላንቲክ ውቅያኖስን ዞረው ለመሄድ በመገደዳቸው በመቶ ሚሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ኪሳራ በእስራኤል ላይ እየደረሰ ነው ።

አላህ ነገሮችን ሁሉ ገለባባጭ ነውና ሀያልነትን በእጃቸው ሊያስገባላቸው ይቻለዋልና ይነስራቸው !! ከፍም ያድርጋቸው !!!

Send as a message
Share on my page
Share in the group