Tarjima qilib boʻlmadi.

በፍጡር መማል

~

በየትኛውም ፍጡር መማል ከሺርክ ነው የሚመደበው። እንኳን በሌላ በመካ አፈር እንኳን መማል አይፈቀድም። ሌላው ቀርቶ በከዕባ እንኳ መማል እንደማይፈቀድ ነብያችን ﷺ ገልፀዋል። [ሶሒሑ ነሳኢይ፡ 3782]

በሌላም ቦታ እንዲህ ብለዋል፦

ألا إن الله ينهاكم أن تحلفوا بآبائكم، من كان حالفا فليحلف بالله، أو ليصمت.

{አዋጅ! አላህ፡ በአባቶቻችሁ እንዳትምሉ ይከለክላችኋል። የሚምል በአላህ ይማል። ያለበለዚያ ዝም ይበል።} [ቡኻሪ፡ 6108] [ሙስሊም፡ 4346]

በተጨማሪም እንዲህ ብለዋል፦ {በአባቶቻችሁ፤ በእናቶቻችሁና ያለአግባብ ሰዎች ለአላህ ብጤዎች ወይም አቻዎች አድርገው በሚይዟቸው አትማሉ። በአላህ እንጂ አትማሉ። እውነተኞች ሆናችሁ እንጂ አትማሉ።} [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 7249]

ሌላው ቀርቶ በነብዩ ዒሳ እንኳን መማል አይፈቀድም። ነብዩ ﷺ {አንዳችሁ በመሲሑ (በዒሳ) ቢምል አደጋ ላይ ወድቋል። መሲሕ ግን ከአባቶቻችሁ የበለጠ ነው} ብለዋል። [አልሙሶነፍ፡ 12278]

መሀላ በፍጡር ከተፈፀመ ሺርክ ይሆናል። ታማኙ ነብይ ﷺ {ከአላህ ሌላ ባለ ነገር የሚማል መሀላ ሁሉ ሺርክ ነው} ይላሉ። [አሶሒሐህ፡ 2042] በሌላ ሐዲሣቸውም እንዲህ ብለዋል፦

من حلف بغير الله فقد كفر أو أشرك

{ከአላህ ሌላ ባለ የማለ በርግጥም ክዷል ወይም አጋርቷል።} [ኢርዋእ፡ 2561]

እዚህም እዚያም እንደዋዛ የምንሰማቸው ወጣ ያሉ መሃላዎች አደጋቸው ምን ያክል የከፋ እንደሆነ ከሶሐቦች ንግግር መረዳት እንችላለን። ዐብዱላህ ብኑ መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፦

لأن أحلف بالله كاذبا أحب إلي من أن أحلف بغيره صادقا

“እውነት ተናግሬ ከአላህ ሌላ ባለ ከምምል ውሸት ተናግሬ በአላህ ብምል እመርጣለሁ።” [ኢርዋእ፡ 2562]

ኢብኑ ዐባስም እንዲሁ “አንድ ጊዜ ከአላህ ሌላ ባለ ምዬ እውነት ከምናገር መቶ ጊዜ በአላህ እየማልኩ ብወነጅል እመርጣለሁ” ይላሉ። [ሸርሑ ሙስሊም፣ነወዊይ፡ 11/105]

ማሳሰቢያ፦

የያዝኩትን ምስል ሙስሊሞች ጭምር እያጋሩት ስላየሁ ነው ማስታወስ የፈለግኩት። ያወራሁት ስለ ሃይማኖቴ ህግ ነው። የዘር ልክፍታችሁን ይዛችሁ እንዳትመጡ።

=

* ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.....Munewor?mibextid=ZbW

* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0....029VaA3X1e5kg7BlsJbo

* ኡማ ላይፍ፦ https://ummalife.com/IbnuMunewor

image
Xabar sifatida yuborish
Sahifamda baham ko'rish
Guruhda ulashish