ሀያእ (አይናፋርነት )
ካላፈርክ ያሻህን ስራ !
حَدَّثَنَا أَحْمَدُ بْنُ يُونُسَ، عَنْ زُهَيْرٍ، حَدَّثَنَا مَنْصُورٌ، عَنْ رِبْعِيِّ بْنِ حِرَاشٍ، حَدَّثَنَا أَبُو مَسْعُودٍ، عُقْبَةُ قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم " إِنَّ مِمَّا أَدْرَكَ النَّاسُ مِنْ كَلاَمِ النُّبُوَّةِ، إِذَا لَمْ تَسْتَحِي فَافْعَلْ مَا شِئْتَ ".
ከአንሷር ጎሳ አባልና በድር ላይ የተዋጉ ከሆኑት አቡ መስኡድ ኡቅባ ኢብኑ አምር ተይዞ የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ- ((ሰዎች ካገኙት ዉስጥ ከቀደምት ነብያዊ ንግግር ዉስጥ ካላፈርክ ያሻህን ስራ!የሚለዉ ነዉ።))ቡኻሪ ዘግበዉታል።(3483)
🔴 ትንሽ ማብራረያ
የዚህን ሐዲስ መልእክት በተመለከተ ከኡለማዎች ሁለት እይታዎች ተንጸባርቀዋል።
👉 አንደኛዉ መልክት-መልክቱ ዛቻ ነዉ የሚል ነዉ።ሰዎች ከጥፋት የሚያቅባቸዉ ሐያእ(አይናፋርነት)ነዉ።የማያፍር ሰዉ ያሻዉን ወንጀልና ብልግና ከመስራት አይመለስም ።ስለዚህ አፍረተ ቢስ በመሆንህ ከጥፋት የማትመለስ ከሆንክ መንገዱ ጨርቅ ያድርግልህ።ግን እወቅ ኋላ የእጅህን ታገኛለህ።
👉 ሁለተኛዉ መልክት -ልትሰራዉ የምትፈልገዉ ስራ ከአላህም ከሰዎችም ዘንድ አሳፋሪ እንዳልሆነ ከተረዳህ መልካም ስራ ነዉና ፈጽመዉ የማል ነዉ።
👉ሀያእ ዋጋዉ አንድ ነገር አይደለም እርግጥ ነዉ ሀያእ በዉስጡ ዉበት አለ ሌሎችም ብዙ ጥቅም አለዉ ለምሳሌ
🔴 ከሐዲሱ የሚወሰዱጨ ቁም ነገሮች-
➡️አይናፋርነት ከጥንት ጀምሮ በቅብብሎሽ ለኛ የተላለፈ ድንቅ ነብያዊ እሴት እንደሆነ
➡️አይናፋርነት የበዛ መልካም ነገሩ የበዛ:እፍረቱ የቀለለ ደግሞ ክፋቱ የበዛ እንደሆነ
➡️ነፍስያዉን ያሰኘዉን ሁሉ ደንታ ሳይሰጥዉ የሚፈጽም ሰዉ እፍረቱ አይናፋርነቱ የተሟጠጠ ደረቅ እንደሆነ ከሐዲሱ እንማራለን።
➡️አይናፋርነት ብዙዎች ከወንጀል የማያቅብ እንደሆነና እፍረትን ማጣት ክፋት ላይ እንደሚጥል ከሐዲሱ እንማራለን።
▶️ሀያእ ለሁለት ይከፈላል
1/ ተፈጥሮዋዊ የሆነ ሀያእ
2/ በትጋት የሚገኝ ሀያእ
▶️ሀያእ ከሁክም አንጻር ለሁለት ይከፈላል
1/የተወደሰ ሀያእ -ኸይር ነዉ የተባለዉ ኢስላም ያዘዘበት ከኢማን ነዉ የተባለዉ
2/ ሸሪአ የሚኮንነዉ ሀያእ አለ
ለምሳሌ -ከማወቅ ወይም ከመጠየቅ ማፈር ይህ የተወገዘ ነዉ ።
▶️ ከአላህ ጋር የሚያያዝ ሀያእና ከፉጡር ጋር የሚያያዝ ሀያእ
ከአላህ ጋር የተያያዘ ሀያእ አላህ ከለከለን ነገር መራቅ ያዘዘንን መታዘዝ ነዉ ።
ከፍጡር ጋር ያለ ሀያእ ሰዎችን እያዩን ጥፋት አለመፈጸም ሰዎችን ምን ይሉኛል ማለት
በመጨረሻም በዚህ ሀዲስ ከሀያእ አንጻር እራሳችን እንፈትሽ በተለይ ማህበራዊ ሚድያ የምንጠቀም እህት ወንድሞች በዋናነት እህቶች ቆም ብለን እራሳችን እንፈትሽ ዛሬ በቲክቶክ በቴሌ ግራም በሌሎችም ማህበራዊ ሚድያ ያለዉ ሁኔታ ያሳፍራልም ያሳዝናልም በተለይ እህቶች ሀያእ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ተረስቶዋል በተለይ በንጽጽር ላይ ያለን እህቶች በዉይይት ስም ልክ ያለፈ ቀልድ :ማላገጥ ከወንድ ጋር የተለያዩ ኢሞጂ(አሻንጉሊት )በመጠቀም በአካል ልትፈጽሚዉ የማትችለዉ የሆኑ ስህተቶች እየተፈጸሙ ነዉና አላህን እንፍራ አላህን እንፍራ!
ከኡስታዝ ኢብኑ ምነዉር አላህ ይጠብቀዉ ደርስ የተወሰደ ።
አቡ አብዱራህማን