1 year Translate
Translation is not possible.

እደለኛ ሰው ማለት.....!

በሌሊቱ ወቅት የሱረቱል በቀራን የመጨረሻ ሁለት አንቀጾች ያነበበ ሰው በአላህ ፍቃድ ሌሊቱን ከመጥፎ ነገር ሁሉ እንደሚጠበቅ ተረድቶ ሲያበቃ አንቀፆቹን አዘወትሮ ያነበባቸው ሰው ነው።

እደለኛ ሰው ማለት.....!

ፈርድ የሆኑ ስላቶችን ከሰገደ በኋላ አያተል ኩርሲይን ካነበበ ጀነትን መግባት ሞት እንጂ ምንም እንደ ማይከለክለው ተረድቶ አዘወትሮ አያተል ኩርሲይን ያነበበ ሰው ነው።

እደለኛ ሰው ማለት.....!

ከመተኛቱ በፊት አያተል ኩርሲይን ያነበበ ሰው ለሊቱን ሙሉ እስኪያነጋ ከአላህ የተመደበ ጠባቂ እንደሚጠብቀውና ሸይጣንም እንደማይቀርበው አውቆ ከመተኛቱ በፊት አያተል ኩርሲይን አዘወትሮ ያነበበ ሰው ነው።

እደለኛ ሰው ማለት.....!

ሱረቱል ኢኽላስን ሶስት ጊዜ ማንበብ ሙሉ ቁርዓንን ከማኽተም ጋር እንደሚስተካከል ተረድቶ ይህችን ሱራ አብዝቶ ያነበበ ሰው ነው።

እደለኛ ሰው ማለት.....!

ለሴትና ለወንድ አማኞች ሁሉ ዱዓዕ ያደረገ ሰው በአያንዳንዱ አማኝ አላህ ዘንድ አጅር እንደሚመዘገብለት ተረድቶ ለሙዕሚኖች ሁሉ አብዝቶ ዱዓዕ ያደረገ ሰው ነው።

እደለኛ ሰው ማለት.....!

ሱብሃነሏህ

ወል ሀምዱ ሊላህ

ወላ ኢላሃ ኢለሏህ

ወሏሁ አክበር

ማለት ፀሀይ ከወጣችበት ሁሉ የተሻለና የበለጠ መሆኑን ተረድቶ እነዚህን ውድ ቃላት አብዝቶና ደጋግሞ ያላቸው ሰው ነው።

እደለኛ ሰው ማለት.....!

ይህንን ካወቀ በኋላ የሰራበትና ሌሌሎችም እንዲያውቁና እንዲተገብሩ በማሰታወስና በማካፈል የአጅሩ ተካፋይ የሆነ ሰው ነው።

Send as a message
Share on my page
Share in the group