Translation is not possible.

ሸይኽ አልባኒ እና ሸይኽ ኢብን ባዝ

አንድ ተማሪ ከሼኽ አልባኒ ጋር በመኪና እየሄደ ነበር ሼይኽ አልባኒም በፍጥነት ነበር የሚነዱት ከዛም ተማሪው እንዲህ አለ..

ተማሪ፦ ያ ሼኽ! ፍጥነታችሁን ቀንሱ ሼኽ ኢብን ባዝ እኮ ከሚፈቀደው ፍጥነት በላይ ማሽከርከር እራስን ለጥፋት እንደመዳረግ ይቆጠራል ብለዋል

አልባኒ፦ ይህ መኪና ነድቶ የማያውቅ ሰው ፈትዋ ነው (ማየት የተሳናቸው ስለነበሩ)

ተማሪው፦ ያላችሁትን ለሼኽ ኢብን ባዝ ልንገራቸው

አልባኒ፦ ንገራቸው

ተማሪውም ሼኽ አልባኒ ያሉትን ለሼኽ ኢብን ባዝ

ሲነግራቸው ሳቁና እንዲህ አሉ ፡ ይህ ዲያ (የግድያ ካሳ) ከፍሎ የማያውቅ ሰው ፈትዋ ነው በለው !

Send as a message
Share on my page
Share in the group