Translation is not possible.

📘ኢብኑል ቀይም ረሂመሁላህ በነቢዩ   ﷺ ሰለዋት ማውረድ ከሚያስገኛቸው  40 ጥቅሞች  ብለው  ከዘረዘሩት መካከል :  

🔸የአላህን ትዕዛዝን መፈፀም ነው።

🔹አስር ደረጃዎችን ከፍ ያደርጋል ።

🔸አሰር ሃሰናትን ያስገኛል ።

🔹ወንጀልን ያሳብሳል።

🔸ዱዓ ተቀባይነት እንዲያገኝ ያደርጋል።

🔹የረስልን ሸፋአ ለማግኘት ይረዳል።

🔸 በነቢዩ ላይ ሰለዋት የሚያበዛ ባሪያ አላህ ሱብሃነሁ ወተአላ ከጭንቁ ይገላግለዋል።

🔹ሰለዋት የሚያበዛ ባሪያ የቂያማ እለት ከነቢዩ ቅርብ እንዲሆን ይደረጋል።

🔸ሃጃውን ሁላ አላህ እንዲያሳካለት ምክንያት  ይሆናል።

🔹የአላህ እዝነትን እንዲያገኝ ያደርጋል።

🔸 ሰለዋት በብዛት የሚያወረድ ሰው ነፍሱ ጥርት ያለች ትሆናለች ።

🔹የረሱልን ሀቅ በጥቂቱ እንደመወጣት ይቆጠራል።

🔸አላህን ከመዘከርና ከማወደስ ይቆጠራል።

🔹ሲራጥ ላይ ለመፅናት  ይረዳል።

🔸ሰለዋት የሚያወርደው ሰው ስም ረሱል ዘንድ ይቀርባል።

🔹ረሱልን በዘውታሪነት ለመውድድ አንዱ መንገድ ነው።

🔸ሰለዋት በሚያወርደው ሰው  በ እድሜውና በስራው ላይ በረከትን ያገኛል።

🔹ንግግርን ና ኹጥባን መቋጫ ይሆናል።

🔸ስስትን ከባሪያው ታርቃለች።

🔹ለንግግር መድረኮች ማማር ና የቂያማ እለት የቁጭት ምክንያት እንዳይሆን ያደርጋል።

🔸ከ ቂያማ ቀን አስደንጋጭ ክስተቶች መዳኛ ይሆናል። 

🔹ጀነት ለመግባት መንገድ ይሆንለታል።

اللهم صل وسلم  وبارك على نبينا محمد  وعلى آله وصحبه أجمعين

Follow & Share → Abubekr Ibn Fulan

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group