Translation is not possible.

🌹ረሱል ﷺ ከሶሃቦቻቸው ጋር ቁጭ ብለው በዱኒያ ላይ በጣም ስለሚዎዷቸው ነገሮች

አየተጨዋወቱ እያሉ ነብዩ ﷺ አቡበክርንረ.ዐ "ያ አባ በከር አንተ በዱኒያ ላይ በጣም የምትወደው

ነገር ምንድነው?" ብለው ጠየቁት።

አቡበክርም  ረ.ዐ "3 ነገሮችን እወዳለሁ:-

1.ከአንቱን ጋር መቀመጥ፣

2.አንቱን ማየት፣

3.አንቱ ባዘዙዋቸው ነገሮች ላይ በሙሉ ገንዘቤን መለገስ" ብሎ መለሰ።

°

ዑመርን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያዑመር ?"

"በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ

1.በድብቅ እንኳን ቢሆን በመልካም ነገር ማዘዝ፣

2.በግልጽ እንኳን ቢሆን ከመጥፎ ነገር መከልከል፣

3 መራራ እንኳን ቢሆን እውነትን መናገር።" ብሎ መለሰ።

°

ዑስማንን ረ.ዐ ጠየቁት "አንተስ ያዑስማን?

በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-

1.ሰዎችን ማብላት፣

2.ሰላምታን ማብዛት፣

3.ሰዎች በተኙ ጊዜ ሶላትን ማብዛት፣

°

አልይን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአልይ ?"

"በዱኒያ ላይ 3ነገሮችን እወዳለሁ:-

1.እንግዳን ማክበር፣

2.በሙቀት ወቅት ፆምን መፆም፣

3.ጠላቴን በሰይፍ መቅላት፣

°

አባ ዘርን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአባ ዘር?"

"በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ :-

1.እርሃብን እወዳለሁ፣

2.በሽታን እወዳለሁ፣

3.ሞትን እወዳለሁ፣

ነብዩም ﷺ "ያ አባ ዘር ለምን እነዚህን ወደድክ?"

አቡዘር መለሰ "ረሃብን ወደድኩት ቀልቤን ፈሪ ሊያደርግልኝ ዘንድ፣

በሽታን ወደድኩት ወንጀሌን ሊያቀልልኝ ዘንድ፣

ሞትን ወደድኩት ከጌታየ ጋር ሊያገናኜኝ ዘንድ።" ብሎ መለሰ።

°

ነብዩ ﷺ " እኔም በዱኒያ ላይ

3 ነገሮችን እወዳለሁ:-

1.ሽቶን እወዳለሁ፣

2.ሚስቶቼን እወዳለሁ፣

3.የአይኔ ማረፊያ ሶላቴን እወዳለሁ፣

በዚህ መካከል ድንገት ጅብሪል አ.ሰ.ወ ዱብ አለ ሰላምታ ካወረደ በኋላ እንዲህ አለ

"አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በዱኒያ ላይ እኔም 3 ነገሮችን እወዳለሁ

ነብዩም ﷺ "ምንድናቸው ያ ጀብሪል?" ብለው ጠየቁት።

1.መልዕክትን ማድረስ፣

2. አማናን አደራን መጠበቅ፣

3.ሚስኪኖችን መውደድ፣

ጅብሪል አ.ሰ.ወ ተመልሶ ወደ ከሄደ በኋላ ረሱልና ﷺ ሱሃቦቻቸው ረዲየሏሁ አጅመኢን ከመቀመጫቸው ሳይነሱ

ተመልሶ መጣና አሁንም ሰላምታውን አቅርቦ:-

"አላህም ሱ.ወ. ሰላም ብሏችኋል ካለ በኋላ አላህም ሱ.ወ እንዲህ ብሏል:-

በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-

1.አላህን አውሺ የሆነችን ምላስ፣

2.አላህን ፈሪ የሆነችን ቀልብ፣

3.መከራ የበዛበት ታጋሽ የሆነችን ጀሰድ።

አላህ ሱ.ወ ታጋሾች አድርጎ ነብዩና ﷺ ሱሃቦች ረ.ዐ.አ የወደዱትን ያስወድደን!

°

Follow & Share →Abubekr Ibn Fulan

↓↓↓↓

Abubekr Ibn Fulan

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group