Translation is not possible.

ኢማም ማሊክ [ረዲየላሁ ዐንሁ] ከምዕራቡ የዐረቢያ ክፍል የመጡት ተማሪያቸው ኢማም የሕያ ኢብኑ የሕያ አል‐ለይሲይን [ረዲየላሁ ዐንሁ] ሲያሰናብቱ እንዲህ መከሯቸው: ‐

«በአራት ንግግሮች እመክርሃለሁ: ‐

⚀ በመጀመሪያው: ‐ የፊቅህ ልሂቃንን እውቀት እሰበስብልሃለሁ። ስለማታውቀው ነገር ስትጠየቅ «አላውቅም» በል።

⚁ በሁለተኛው: ‐ የጠቢባንን ጥበብ እሰበስብልሃለሁ። ከሰዎች ጋር ስትቀመጥ ከሁሉም በላይ ዝምተኛ ሁን። በሚናገሩት ነገር ላይ ትክክል ሆነው ከተገኙ አንተም ከነሱ ጋር ትክክል ትሆናለህ። ከተሳሳቱም አንተ ዳንክ።

⚂ በሦስተኛው: ‐ የሃኪሞችን ህክምና እሰበስብልሃለሁ። እጅህን ወደ ምግብ ስትሰነዝር እየፈለግከው ሰንዝር፤ እጅህን ስትሰበስብም እየፈለግከው ሰብስብ። ይህንን ካደረግክ ከሞት በሽታ በስተቀር ሌላ በሽታ አያገኝህም።

⚃ አራተኛው ጥበብ ነው: ‐ አንጀት ሲሞላ ሃሳብ ይተኛል። አካልም ዒባዳውን ትቶ ያንቀላፋል።

📖 «ዘህሩል‐አከም ፊል‐አምሳሊ ወል‐ሒከም» ፥ ገፅ 63

Send as a message
Share on my page
Share in the group